ዝናው ፡ ይወራ (Zinaw Yiwera) - ሳሙኤል ፡ ተስፋሚካአኤል

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search
ሳሙኤል ፡ ተስፋሚካአኤል
(Samuel Tesfamichael)

፬
(4)

መልህቄ
(Melhike)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፲ ፬ (2022)
ቁጥር (Track):

፩ (1)

ርዝመት (Len.): 6:36
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሳሙኤል ፡ ተስፋሚካአኤል ፡ አልበሞች
(Albums by Samuel Tesfamichael)

ዝናውን ፡ ለሰማው ፡ እጅግ ፡ ያስፈራል
ባለዝና ፡ እንደሱ ፡ ከየት ፡ ይገኛል
በዘመናት ፡ መሃል ፡ ይታወቃል
ብቻውን ፡ የበላይ ፡ ሆኖ ፡ ይኖራል

እግዚአብሔር /4

እግዚአብሔርን ፡ ከእኔ ፡ ጋራ
ታላቅ ፡ አርጉት ፡ ዝናው ፡ ይወራ
ይወራ ፡ ዝናው ፡ ይወራ/2
በምድር ፡ ሁሉ ፡ ይወራ
ይወራ ፡ ዝናው ፡ ይወራ
በአለም ፡ ሁሉ ፡ ይወራ
ይወራ ፡ ዝናው ፡ ይወራ

አንጎዳጎደ ፡ ልኡል ፡ ቃሉን ፡ ሰጠ
በክብሩ ፡ ሲቆም ፡ ምድርን ፡ አናወጠ
የዘላለም ፡ ተራሮች ፡ ተፈረካከሱ
የጥንትም ፡ ኮረብቶች ፡ ወዲያ ፡ ፈራረሱ
ከሚንቦገቦገው ፡ ፀዳል ፡ የተነሳ
ፍላፆች ፡ ከወጡበት ፡ ብርሃን ፡ የተነሳ
ጨረቃ ፡ እና ፡ ፀሃይ ፡ በቦታቸው ፡ ቆሙ
በክብሩ ፡ ነፀብራቅ ፡ እየተደመሙ

ክብሩ ፡ ሰማያትን ፡ ሁሉ ፡ የሸፈነ
ስሙም ፡ በምድር ፡ የተመሰገነ
ለታላቅነቱ ፡ ፍፃሜ ፡ የሌለው
በዘመናት ፡ መሃል ፡ እርጅና ፡ የማያውቀው
ከዋክብት ፡ ታዘዙ ፡ በህዋ ፡ አበሩ
በአፍንጫው ፡ እስትንፋስ ፡ ውሆች ፡ ተከመሩ
ትልቅ ፡ የሚለው ፡ ቃል ፡ ፍፁም ፡ የማይገልፀው
እጅጉን ፡ ያፈራል ፡ ዝናውን ፡ ለሰማው