በመድህኔ (Bemedine) - ሳሙኤል ፡ ተስፋሚካአኤል

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search
ሳሙኤል ፡ ተስፋሚካአኤል
(Samuel Tesfamichael)

፬
(4)

መልህቄ
(Melhike)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፲ ፬ (2022)
ቁጥር (Track):

፬ (4)

ርዝመት (Len.): 6:55
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሳሙኤል ፡ ተስፋሚካአኤል ፡ አልበሞች
(Albums by Samuel Tesfamichael)

በእኔ ፡ ፈንታ ፡ ተተክቶ
ወጥቻለው ፡ እስሬ ፡ ተፈቶ
በሃጥያቴ ፡ ምክንያት ፡ እንዳልቀጣ
ክርስቶስ ፡ እየሱስ ፡ ክብሩን ፡ ትቶ ፡ መጣ

እዳዬንም ፡ እሱ ፡ ከፍሎልኛል
ነፃ ፡ ሰው ፡ ነኝ ፡ ዋሴ ፡ ሆኖልኛል
አድራሻዬ ፡ በሰማዩ ፡ ስፍራ
አድርጎታል ፡ ከእግዚአብሔር ፡ ጋራ

ኩነኔ ፡ የለብኝም ፡ አሁን ፡ ኩነኔ
ነፃ ፡ ወጥቻለው ፡ በመድህኔ

ምንም ፡ ሳላደርግ ፡ ምንም ፡ ሳልስራ
በአብ ፡ ቀኝ ፡ ተቀመጥኩ ፡ ከእየሱሴ ፡ ጋራ
ምንም ፡ ሳልከፍል ፡ ያለምንም ፡ ዋጋ
የዘላለም ፡ ህይወት ፡ አገኘው ፡ በፀጋ
እንዲሁ ፡ በፀጋ/2
የዘላለም ፡ ህይወት ፡ አገኘው ፡ በፀጋ

ራሱ ፡ ሰጠ ፡ ለኔ ፡ ሊገረፍ
አንድም ፡ ጅራፍ ፡ በኔ ፡ ላይ ፡ እንዳያርፍ
መራራውን ፡ ፅዋ ፡ እንዳልጠጣው
አበሳዬ ፡ ወስዶ ፡ ጨረሰው

የአለምን ፡ ሃጥያት ፡ ሚያስወግደው
የእግዚአብሔር ፡ በግ ፡ በደሌን ፡ ሰቀለው
በራሱ ፡ ደም ፡ ይዞኝ ፡ አብ ፡ ጋር ፡ ገባ
አለበሰኝ ፡ ፀጋውን ፡ እንደ ፡ ካባ