ፈጣሪ (Fetari) - ሳሙኤል ፡ ተስፋሚካአኤል

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search
ሳሙኤል ፡ ተስፋሚካአኤል
(Samuel Tesfamichael)

፬
(4)

መልህቄ
(Melhike)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፲ ፬ (2022)
ቁጥር (Track):

፲ (10)

ርዝመት (Len.): 4:33
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሳሙኤል ፡ ተስፋሚካአኤል ፡ አልበሞች
(Albums by Samuel Tesfamichael)

አምናለው ፡ ዛሬም ፡ በዚህ ፡ አለህ
አምናለው ፡ ዛሬም ፡ ትሰራለህ

አንተ ፡ ብቻነህ ፡ ፈጣሪ ፡ ብቻህን ፡ ፈጣሪ
ጀማሪ ፡ ፈጣሪ ፡ የሁሉ ፡ ፈጣሪ

ይሁን ፡ ይሁን ፡ ብለህ
ፍጥረታትን ፡ በቃልህ ፡ ፈጠርህ
መጥቶልሃል ፡ ያልነበረው
አቤት ፡ ብሎሃል ፡ የማይሰማው
አንተ ፡ ያልከው ፡ የቀረ ፡ የለም
ፀንቶልሃል ፡ በቃልህ ፡ ሁሉም

የሰማይ ፡ ምድሩ ፡ የውቅያኖሱ
የሚበሩ ፡ ሚንቀሳቀሱ
ፈጥረህ ፡ ብቻ ፡ መቼ ፡ ተውካቸው
መልካም ፡ ነው ፡ ብለህ ፡ ባርካቸው
የህያዋን ፡ ምንጭ ፡ ህይወት ፡ ጀማሪ
የግኡዛን ፡ ደግሞ ፡ ፈጣሪ

ማን ፡ ነበረና ፡ ሊያማክርህ
አንተ ፡ ብቻህን ፡ ሁሉን ፡ ፈጣሪ
ያላማካሪ ፡ ብቻህን ፡ ሰሪ
እግዚአብሔር ፡ ነህ ፡ ሁሉን ፡ ፈጣሪ