ትመለካለህ (Timelekaleh) - ሳሙኤል ፡ ተስፋሚካአኤል

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search
ሳሙኤል ፡ ተስፋሚካአኤል
(Samuel Tesfamichael)

፬
(4)

መልህቄ
(Melhike)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፲ ፬ (2022)
ቁጥር (Track):

፰ (8)

ርዝመት (Len.): 5:28
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሳሙኤል ፡ ተስፋሚካአኤል ፡ አልበሞች
(Albums by Samuel Tesfamichael)

ገና ፡ ሰማይ ፡ እና ፡ ምድር ፡ ሳይፈጠር
ገና ፡ አማልክት ፡ የሚባል ፡ ሌላ ፡ ሳይኖር
ብቻህን ፡ በክብር ፡ ዙፋን ፡ ላይ ፡ ተቀምጠህ
ትመለካለህ

ገና ፡ ሰማይ ፡ እና ፡ ምድር ፡ ሳይታሰቡ
ገና ፡ ነፋሳት ፡ ሳይወጡ ፡ ከመዛግቡ
በአእላፋት ፡ መላእክት ፡ ቀን ፡ ከሌት ፡ ተከበህ
ትመለካለህ/ 8x

ክብር ፡ የሚለው ፡ ቃል ፡ ሌላ ፡ ሳይከብርበት
አንተ ፡ ክብር ፡ ጠግበህ ፡ ዘላለም ፡ ኖርክበት
ክብር ፡ የሚለው ፡ ቃል ፡ ማንም ፡ ሳይከብርበት
አንተ ፡ ክብርን ፡ ጠግበህ ፡ ዘላለም ፡ ኖርክበት
ክብር ፡ ማለት ፡ የሚያውቀው ፡ አንተን ፡ ነው
መጀመርያ ፡ የታወቀው ፡ ባንተ ፡ ነው

እናመልክሃለን ፡ እግዚአብሔር