ትለያለህ (Tileyaleh) - ሳሙኤል ፡ ተስፋሚካአኤል

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search
ሳሙኤል ፡ ተስፋሚካአኤል
(Samuel Tesfamichael)

፬
(4)

መልህቄ
(Melhike)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፲ ፬ (2022)
ቁጥር (Track):

፪ (2)

ርዝመት (Len.): 6:17
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሳሙኤል ፡ ተስፋሚካአኤል ፡ አልበሞች
(Albums by Samuel Tesfamichael)

የክብር ፡ ንጉስ ፡ ሆይ ፡ እንዴት ፡ ታላቅ ፡ ነህ
ከዙፋንህ ፡ ስር ፡ በእውነት ፡ በመንፈስ ፡ ልስገድልህ

ከሰው ፡ ልጆች ፡ ይልቅ ፡ ያማረ ፡ ውበትህ
የፀጋ ፡ ቃል ፡ ሁሌ ፡ ያፈሳል ፡ ከንፈርህ
አይኖቼ ፡ አይተውህ
ፈዘዙ ፡ በክብርህ /2

ማን ፡ ሊመስልህ
አረ ፡ ማን ፡ ሊያክልህ
አንተ ፡ እኮ ፡ ከአማልክት ፡ ትለያለህ
ውዴ ፡ ከአእላፋት ፡ ትበልጣለህ

ፊትህ ፡ እንደ ፡ ፀሃይ ፡ በሃይል ፡ ያበራል
እንደ ፡ ብዙ ፡ ውሆች ፡ ድምፅህም ፡ ያስፈራል
በግርማህ ፡ ተገረሜ
ቀረሁኝ ፡ ተደምሜ

ማን ፡ ሊመስልህ
አረ ፡ ማን ፡ ሊያክልህ
አንተ ፡ እኮ ፡ ከአማልክት ፡ ትለያለህ
ውዴ ፡ ከአእላፋት ፡ ትበልጣለህ

ሃሌሉያ/8