አመለጠች ፡ ነፍሴ (Ameletech Nefse) - ሳሙኤል ፡ ተስፋሚካአኤል

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search
ሳሙኤል ፡ ተስፋሚካአኤል
(Samuel Tesfamichael)

፬
(4)

መልህቄ
(Melhike)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፲ ፬ (2022)
ቁጥር (Track):

፲ ፮ (16)

ርዝመት (Len.): 6:42
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሳሙኤል ፡ ተስፋሚካአኤል ፡ አልበሞች
(Albums by Samuel Tesfamichael)

እግዚአብሔር ፡ ባይራራልኝ
ልጁን ፡ ልኮ ፡ ባይታደገኝ
የጠላት ፡ ሴራ ፡ ወጥመድ ፡ ዘርግቶብኝ
በሙታን ፡ ሰፈር ፡ እዛው ፡ ላይ ፡ በቀረሁኝ

ግን ፡ አልተሳካም ፡ አልሆነለትም
ነፍሴ ፡ ከቶ ፡ አላገኛትም
በክርስቶስ ፡ በተሰራው ፡ ስራ
አመለጠች ፡ እንደወፍ ፡ በራ

አመለጠች/4
ነፍሴ ፡ እንደወፍ ፡ ከአዳኞች ፡ ወጥመድ ፡ አመለጠች

በርራ ፡ በርራ ፡ እንደ ፡ ወፍ ፡ በርራ /2
አመለጠች ፡ በርራ /2
በክርስቶስ ፡ ስራ
አመለጠች ፡ በርራ
በመስቀል ፡ ላይ ፡ ስራ
አመለጠች ፡ በርራ

አዳኙ ፡ በስውር ፡ ወጥመድ ፡ አስቀመጠ
ከአሁን ፡ አሁን ፡ ያዘልኝ ፡ ሲል ፡ አይኑ ፡ እንዳፈጠጠ
አዳኜ ፡ ሲመጣ ፡ ወጥመዱን ፡ ሲረግጠው
ነፍሴን ፡ አስመልጦ ፡ ቀንበሩን ፡ ሰባበረው /4

እንዲህን ፡ ነው ፡ ያመለጠችው ፡ ነፍሴ/2
እንደወፍ ፡ አመለጠች ፡ ነፍሴ /2
በረረች ፡ አመለጠች ፡ ነፍሴ /2
በአዳኝዋ ፡ በኢየሱሴ/4
በኢየሱሴ

ሞትና ፡ ሲኦል ፡ አንድ ፡ ላይ ፡ ተስማምተው
ዘላለሜን ፡ ሊያደርጉት ፡ በድቅድቅ ፡ ጨለማው
የትንሳኤው ፡ ጉልበት ፡ ሞትን ፡ ራሱን ፡ ገድሎት
መውጊያውን ፡ ሰባብሮ ፡ ነፍሴ ፡ አስመለጣት/4

እንዲህን ፡ ነው ፡ ያመለጠችው ፡ ነፍሴ/2
እንደወፍ ፡ አመለጠች ፡ ነፍሴ /2
በረረች ፡ አመለጠች ፡ ነፍሴ /2
በአዳኝዋ ፡ በኢየሱሴ/4
በኢየሱሴ