ኢየሱስ ፡ ድል ፡ ነሳ (Eyesus Dil Nesa) - ሳሙኤል ፡ ተስፋሚካአኤል

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search
ሳሙኤል ፡ ተስፋሚካአኤል
(Samuel Tesfamichael)

፬
(4)

መልህቄ
(Melhike)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፲ ፬ (2022)
ቁጥር (Track):

፲ ፬ (14)

ርዝመት (Len.): 7:00
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሳሙኤል ፡ ተስፋሚካአኤል ፡ አልበሞች
(Albums by Samuel Tesfamichael)

የጌቶች ፡ ጌታ ፡ ነው
እየሱስ ፡ የማመልከው
መፅሃፉን ፡ ወስዶ ፡ ማህተሙን ፡ የፈታ
የነገስታት ፡ ንጉስ ፡ የጌቶቹ ፡ ጌታ
ከይሁዳ ፡ ነገድ ፡ የሆነው ፡ አንበሳ
ገናናው ፡ ኢየሱስ ፡ ብቻውን ፡ ድል ፡ ነሳ

ከእርሱ ፡ ጋራ ፡ ሊሰለፉ
የወደዱ ፡ ሁሉ ፡ አለፉ
ኢየሱስ ፡ ግን ፡ አለ ፡ በዙፋኑ
በማእረጉ ፡ በስልጣኑ

የለም ፡ የለም
እንደርሱ ፡ ያለ ፡ የለም
በሰማይ ፡ የለም ፡ በምድር ፡ የለም/2

የከፈተውን ፡ ማን ፡ ይዘጋዋል
የዘጋውን ፡ ማን ፡ ይከፍተዋል
ተውባይ ፡ ከልካይ ፡ አንድ ፡ እንኩዋን ፡ የሌለው
ቁልፉ ፡ እሱ ፡ እጅ ፡ ብቻ ፡ ነው

ከዘላለም ፡ እስከ ፡ ዘላለም
ህያው ፡ ሆኖ ፡ የሚኖር ፡ እንደርሱ ፡ የለም
ከነገድ ፡ ከቁዋንቁ ፡ ህዝቡን ፡ የዋጀው
የታርደው ፡ በግ ፡ እርሱ ፡ ብቻ ፡ ነው