From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation
Jump to search
ክንዳችሁ ፡ አይላላ
ጉልበታችሁ ፡ አይበላ
የእስራኤል ፡ አምላክ ፡ አለ ፡ ከእኛ ፡ ጋራ
የናዝሬቱ ፡ እየሱስ ፡ አለ ፡ ከእኛ ፡ ጋራ
ከግብፅ ፡ ከባርነት ፡ ከፈርዖን ፡ ብዛት
ህዝቡን ፡ ያሳረፈ ፡ ከጭንቀት ፡ ከፍርሃት
በእሳት ፡ በደመና ፡ በቀን ፡ ሌት ፡ የመራ
ያው ፡ የእስራኤል ፡ አምላክ ፡ አለ ፡ ከእኛ ፡ ጋራ
መንገዱ ፡ እጅግ ፡ እሩቅ ፡ ቢመስል ፡ ሚከብድ ፡ ማያልቅ
የአለም ፡ ኑሮ ፡ ፈተና ፡ ቢሆንም ፡ ትንቅንቅ
ከእኛ ፡ ጋራ ፡ ያለው ፡ አለምን ፡ አሸንፏል
እስከ ፡ ፅዮን ፡ ድረስ ፡ በድል ፡ ይመራናል
ክንዳችሁ ፡ አይላላ
ጉልበታችሁ ፡ አይበላ
የእስራኤል ፡ አምላክ ፡ አለ ፡ ከእኛ ፡ ጋራ
አማኑኤል ፡ እርሱ ፡ አለ ፡ ከእኛ ፡ ጋራ
ከእግዚአብሔር ፡ ጋር ፡ ሆነው ፡ የወጡ ፡ ወደ ፡ ሰልፉ
የአንበሶችን ፡ አፍ ፡ ዘጉ ፡ የእሳትን ፡ ሃይል ፡ አጠፉ
በቅንም ፡ ፈረዱ ፡ መንግስታቱን ፡ ድል ፡ ነሱ
አለምን ፡ ኮነኑ ፡ ጣኦትን ፡ አፈረሱ
ዛሬም ፡ ከበውናል ፡ እነርሱ ፡ እንደደመና
ክንዳችን ፡ እንዳይላላ ፡ ጉልበታችን ፡ ይፅና
የፃድቅ ፡ ጉልበቱ ፡ ነውና ፡ እምነቱ
ቅዱሳን ፡ ካህናቱ ፡ እልፍ ፡ በሉ ፡ በርቱ
ክንዳችሁ ፡ አይላላ
ጉልበታችሁ ፡ አይበላ
የእስራኤል ፡ አምላክ ፡ አለ ፡ ከእኛ ፡ ጋራ
ተስፋውን ፡ የሰጠው ፡ አለ ፡ ከእኛ ፡ ጋራ
ሃይልን ፡ በሚሰጠን ፡ ሁሉን ፡ እንችላለን
በወደደን ፡ በእርሱ ፡ ከአሸናፊዎች ፡ እንበልጣለን
ክንዳችን ፡ ይበርታ ፡ ጉልበታችን ፡ ይፅና
አምላካችን ፡ ብርቱ ፡ ሁሉን ፡ ቻይ ፡ ነውና
|