እታመናለሁ (Etamenihalew) - ሳሙኤል ፡ ተስፋሚካአኤል

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search
ሳሙኤል ፡ ተስፋሚካአኤል
(Samuel Tesfamichael)

፬
(4)

መልህቄ
(Melhike)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፲ ፬ (2022)
ቁጥር (Track):

፮ (6)

ርዝመት (Len.): 6:08
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሳሙኤል ፡ ተስፋሚካአኤል ፡ አልበሞች
(Albums by Samuel Tesfamichael)

የታመነህ ፡ ሰው ፡ እንደንጋት ፡ ብርሃን ፡ ህይወቱ ፡ ይደምቃል
የታመነህ ፡ ሰው ፡ ሙሉ ፡ ቀን ፡ እኪሆን ፡ ጨምሮ ፡ ያበራል
አንተን ፡ ያመነ ፡ አይፈራ ፡ አይደነግጥ ፡ በለሊቱ
አንተን ፡ ያመነ ፡ ቃልህ ፡ ይሆንለታል ፡ ለእግሩ ፡ መብራቱ

የሚጤሰውን ፡ ጥዋፍ ፡ አታጠፋምና
ቅጥቅጡን ፡ ሸንበቆ ፡ አትሰብርምና
ስለዚህ ፡ አይኔን ፡ ወዳንተ ፡ ላቅና
ስለዚህ ፡ ልቤን ፡ ባንተ ፡ ላፅና

አይኔን ፡ አቀናለሁ
ልቤን ፡ አፀናለሁ
አንተኑ/2 እታመንሃለው
አንተኑ/2 እደገፍሃለው
እግዚአብሔር ፡ አለቴ ፡ እታመንሃለው
አምባ ፡ መድሃኒቴ ፡ እደገፍሃለው

የታመነህ ፡ ሰው ፡ በወንዝ ፡ ዳር ፡ እንዳለ ፡ ዛፍ ፡ ይሆናል
የታመነህ ፡ ሰው ፡ ሁሌ ፡ ይለመልማል ፡ ሁሌም ፡ ያፈራል
አንተን ፡ ያመነ ፡ ዙሪያው ፡ ደረቅ ፡ ቢሆን ፡ ምድረበዳ
አንተን ፡ ያመነ ፡ ለሌላው ፡ ይተርፋል ፡ አይሆንም ፡ ባለ ፡ እዳ

የታመነህ ፡ ሰው ፡ ቃልህን ፡ ይሰማል ፡ ደግሞም ፡ ያደርጋል
የታመነህ ፡ ሰው ፡ በፀናው ፡ አለት ፡ ላይ ፡ ቤቱን ፡ ይሰራል
አንተን ፡ ያመነ ፡ ዝናብ ፡ ጎርፍ ፡ ንፋሱ ፡ መጥቶ ፡ ቢገፋው
አንተን ፡ ያመነ ፡ አልፎት ፡ ይሄዳል ፡ እንጂ ፡ ጫፉን ፡ አ