እድለኛ (Edilegna) - ሳሙኤል ፡ ተስፋሚካአኤል

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search
ሳሙኤል ፡ ተስፋሚካአኤል
(Samuel Tesfamichael)

፬
(4)

መልህቄ
(Melhike)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፲ ፬ (2022)
ቁጥር (Track):

፫ (3)

ርዝመት (Len.): 6:08
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሳሙኤል ፡ ተስፋሚካአኤል ፡ አልበሞች
(Albums by Samuel Tesfamichael)

አንተ ፡ ባለህበት ፡ በከበረው ፡ ስፍራ
ካንተ ፡ ጋራ ፡ ልኖር ፡ ስምህን ፡ እንድጠራ
እድሉን ፡ አገኘው ፡ በቤትህ ፡ ልቀድስ
እጥፍ ፡ ልስገድልህ ፡ ነፍሴን ፡ ፊትህ ፡ ላፍስስ
እንዴት ፡ መታደል ፡ ነው ፡ ስምህን ፡ መጥራቱ
ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ ማለቱ
የተመረጠ ፡ ስም ፡ ከስም ፡ ሁሉ ፡ በላይ
አይኔን ፡ አድርጎታል ፡ ካንተ ፡ ሌላ ፡ እንዳላይ

የህይወቴ ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነህ
ኢየሱስ ፡ የኑሮዬ ፡ ኢየሱስ ፡ ንጉስ ፡ ነህ
ኢየሱስ ፡ መአዛህን ፡ ኢየሱስ ፡ ስወደው
ኢየሱስ ፡ መገኘትህ ፡ ኢየሱስ ፡ ህይወቴ ፡ ነው

ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ ወደድኩህ
ከእልፍ ፡ ከአእላፋት ፡ መረጥኩህ
ውዴ ፡ ከእንቁ ፡ ትበልጣለህ
ከማር ፡ ወለላ ፡ ትጣፍጣለህ
እረ ፡ እንዴት ፡ እድለኛ ፡ ነኝ
በፊትህ ፡ ሞገስን ፡ አገኘሁኝ
የኔ ፡ ብቻ ፡ አይበቃም ፡ ዝማሬ
ይገዛልህ ፡ ዘር ፡ ማንዘሬ

የቤትህ ፡ ስርአት ፡ በሚደረግበት
ህዝቡም ፡ መላእክቱም ፡ ቅዱስ ፡ በሚሉበት
እድሉን ፡ አገኘው ፡ ዘላለም ፡ ላመልክህ
ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ እያልኩ ፡ ከቅዱሳንህ
እንዴት ፡ መታደል ፡ ነው ፡ ዘላለም ፡ ማምለኬ
ጎንበስ ፡ ቀና ፡ እያልኩ ፡ ፊትህ ፡ ተንበርክኬ
በማይነገር ፡ ክብር ፡ በሚደነቅ ፡ ብርሃን
ላይህ ፡ ጉዋጉቻለው ፡ ውዴ ፡ ኢየሱስ ፡ አንተን

ኢየሱስ ፡ ሙሽራዬ ፡ ኢየሱስ ፡ ቶሎ ፡ ና
ኢየሱስ ፡ መናፈቄ ፡ ኢየሱስ ፡ በዝትዋልና
ኢየሱስ ፡ ማዶ ፡ ማዶ ፡ ኢየሱስ ፡ ማዶ ፡ እያየው
ኢየሱስ ፡ አማትሬ ፡ ኢየሱስ ፡ እጠብቅሃለው