መልህቄ (Melihke) - ሳሙኤል ፡ ተስፋሚካአኤል

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search
ሳሙኤል ፡ ተስፋሚካአኤል
(Samuel Tesfamichael)

፬
(4)

መልህቄ
(Melhike)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፲ ፬ (2022)
ቁጥር (Track):

፱ (9)

ርዝመት (Len.): 6:10
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሳሙኤል ፡ ተስፋሚካአኤል ፡ አልበሞች
(Albums by Samuel Tesfamichael)

ነፋሱ ፡ ቢነፍስ ፡ ወጀቡ ፡ ቢያጉዋራ
በበዛው ፡ ሰላምህ ፡ አለህ ፡ ከኔ ፡ ጋራ
አለም ፡ ብትናወት ፡ ማእበሉ ፡ ቢበዛ
ነፍሴ ፡ እርፍ ፡ አለች ፡ በፍቅርህ ፡ ተይዛ

የዘላለሜ ፡ ነህ ፡ ሁሉ ፡ ሲቀር ፡ ኃላ
መልህቅ ፡ የሆንከኝ ፡ ግራ ፡ እንዳልጋባ

መልህቄ/2x/
ያዝከኝ ፡ ኢየሱሴ

የፍቅርህ ፡ ሰንሰለት ፡ አጥብቆ ፡ ይዞኛል
እኔ ፡ ብደክምበት ፡ መቼ ፡ ይተወኛል
በሞትህ ፡ ወደ ፡ ታች ፡ ወርደህ ፡ መልህቄ ፡ ያዝከኝ
ልዩ ፡ ፍጥረት ፡ ቢሆን ፡ ሞትም ፡ እንዳይለኝ

እንደ ፡ ነፍስ ፡ መልህቅ ፡ በሆነ ፡ ተስፋ
እርግጥ ፡ እና ፡ ፅኑ ፡ መቼም ፡ የማይጠፋ
በዚህኛው ፡ ቢሆን ፡ በወዲያኛው ፡ አለም
ጥብቅ ፡ አርገህ ፡ ያዝከኝ ፡ እስከለዘላለም