አርነት ፡ አለ (Arinet Ale) - ሳሙኤል ፡ ተስፋሚካአኤል

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search
ሳሙኤል ፡ ተስፋሚካአኤል
(Samuel Tesfamichael)

፬
(4)

መልህቄ
(Melhike)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፲ ፬ (2022)
ቁጥር (Track):

፲ ፫ (13)

ርዝመት (Len.): 6:48
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሳሙኤል ፡ ተስፋሚካአኤል ፡ አልበሞች
(Albums by Samuel Tesfamichael)

አርነት ፡ አለ ፡ አንተ ፡ ባለህበት
መፈታት ፡ አለ ፡ አንተ ፡ ባለህበት

ስምህ ፡ ሲጠራ ፡ ኢየሱስ ፡ ሲባል
ደዌ ፡ ይፈወሳል ፡ አጋንንት ፡ ይርቃል/ይሸሻል
ያዘነው ፡ ይፅናናል ፡ በደስታ ፡ ይሞላል
የስምህ ፡ ጉልበት ፡ ይህንን ፡ ያደርጋል

ልብን ፡ የምትፈውስ
ነፍስን ፡ የምትመልስ
ሰባራውን ፡ የምትጠኝ
አንተ ፡ ብቻ ፡ ነህ ፡ ኢየሱስ

ኢየሱስ/4ስምህ ፡ ሲጠራ ፡ ኢየሱስ ፡ ሲባል
ጥያቄ ፡ ይመለሳል ፡ ቁዋጠሮ ፡ ይፈታል
ደካማው ፡ ይበረታል ፡ ታምራት ፡ ይሆናል
የስምህ ፡ ጉልበት ፡ ይህንን ፡ ያደርጋል