From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation
Jump to search
|
|
ሃና ፡ ተክለ (Hana Tekle)
|
|
|
|
፬ (4)
|
መሥዋዕት (Meswaet)
|
| ዓ.ም. (Year):
|
2024
|
| ቁጥር (Track):
|
፬ (4)
|
| ርዝመት (Len.):
|
4:34
|
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች (Other Songs in the Album)
|
|
|
የሃና ፡ ተክለ ፡ አልበሞች (Albums by Hana Tekle)
|
|
|
ከተከሸኑ ፡ እልፍ ፡ ቃላት
ከተመረጠ ፡ የቅኔ ፡ ብዛት
ሃገሩን ፡ ከሞላው ፡ ዜማ
የኔ ፡ ሕይወት ፡ ላንተ ፡ ይሰማ/ይሠዋ
ቢዘምርልህ ፡ ይህ ፡ አንደበቴ
መልክህ ፡ በራቀው ፡ የዕለት ፡ ዕለት ፡ ሕይወቴ
መሥዋዕቴ ፡ ላንተ ፡ እኮ ፡ ነው
የሌለህበት ፡ ላንተ ፡ ምንህ ፡ ነው
መሥዋዕቴ ፡ ላንተ ፡ እኮ ፡ ነው
ያልከበርክበት ፡ ሁሉ ፡ ድካም ፡ ነው
ይዘምር ፡ የእልፈኝ ፡ ሕይወቴ
አምልኮዬ ፡ ይቅደም ፡ በቤቴ
ሊሁነው ፡ የዘመርቁትን
በቃላት ፡ ያሰፈርኩትን
ያምልክህ ፡ የጓዳ ፡ ሕይወቴ
ይዘምር ፡ ይቅደም ፡ በቤቴ
ሊሁነው ፡ የዘመርኩትን
በዜማ ፡ ያመለኩትን
ላምልክህ ፡ በሕይወቴ
ይገዛ ፡ መላው ፡ እኔነቴ
ላምልክህ ፡ በሕይወቴ
ያምልክህ ፡ መላው ፡ ሰውነቴ
ላምልክህ ፡ በሕይወቴ
ላንተ ፡ መሥዋዕት ፡ ይህ/ንፁህ ፡ አይደል ፡ ወይ
ያንተ ፡ ምስጋና ፡ ህይወት ፡ አይደል ፡ ወይ
ያምልክህ ፡ መላው ፡ እኔነቴ/ሰውነቴ
ላምልክህ ፡ በሕይወቴ
ይዘምር ፡ ሕይወቴ
ላምልክህ ፡ በሕይወቴ
መስዋዕቴ ፡ ላንተ ፡ ነው
|