አልፍ ፡ ዕዳ (Elf Eda) - ሃና ፡ ተክለ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search
ሃና ፡ ተክለ
(Hana Tekle)

፬
(4)

መሥዋዕት
(Meswaet)

ዓ.ም. (Year): 2024
ቁጥር (Track):

፲ ፭ (15)

ርዝመት (Len.): 6:02
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሃና ፡ ተክለ ፡ አልበሞች
(Albums by Hana Tekle)

ምስጋና ፡ የሚሠዋ ፡ እርሱ ፡ ያከብረኛል
ማዳኔን ፡ የማሳይበት ፡ በዚያ ፡ ድል ፡ ይገኛል
ይህን ፡ ጌታ ፡ ብለሀልና
ይኸው ፡ ከልቤ ፡ ምስጋና
እግዚአብሔር ፡ የተገባህ
በምስጋና ፡ የተፈራህ

ባለፍኩበት ፡ መንገድ ፡ እጅህን ፡ ብዙ ፡ አየሁ
የውለታህን ፡ ቁጥር ፡ አልችልም ፡ ልገልፀው
ብዙ ፡ ብዙ ፡ ዋልህ ፡ ይህን ፡ አልዘነጋም
ያረግክልኝ ፡ ሁሉ ፡ ከልቤ ፡ አይጠፋም

እልፍ ፡ ዕዳ ፡ አለብኝ ፡ የምስጋና
እልፍ ፡ ዕዳ ፡ አለብኝ ፡ የእልልታ/የውለታህ
እልፍ ፡ ዕዳ ፡ አለብኝ ፡ የዝማሬ
እልፍ ፡ ዕዳ ፡ አለብኝ የውዳሴ

ባያደርስልኝም ፡ የልቤን ፡ በሙሉ
ምስጋና ፡ ነው ፡ መልሴ ፡ ላረክልኝ ፡ ሁሉ
በመልካምነትህ ፡ ቤቴን ፡ ሞልተኸዋል
ከምስጋና ፡ በቀር ፡ ምን ፡ ብል ፡ ይገልፅሀል

ብዙ ፡ ዕዳ ፡ አለብኝ ፡ የምስጋናህ
ብዙ ፡ ዕዳ ፡ አለብኝ ፡ የውለታህ
እልፍ ፡ ዕዳ ፡ አለብኝ ፡ የምስጋና
እልፍ ፡ ዕዳ ፡ አለብኝ ፡ የእልልታ/የውለታህ
እልፍ ፡ ዕዳ ፡ አለብኝ ፡ የዝማሬ
እልፍ ፡ ዕዳ ፡ አለብኝ የውዳሴ

ካልተደረገልኝ ፡ ይልቅ ፡ የተደረገልኝ ፡ ስንቱ ፡ ነው
እኔ ፡ አልሆነልኝም ፡ ከምለው ፡ ይልቅ ፡ የሆነልኝ ፡ እጅግ ፡ ብዙ ፡ ነው
ዛሬም ፡ ጥያቄዬን ፡ ይዤ ፡ ለምስጋና ፡ ልቤ ፡ አይዘገይም
በስምህ ፡ ስንቱን ፡ አልፌያለሁ ፡ ይህንን ፡ ከልቤ ፡ አልፍቀውም

እልፍ ፡ ዕዳ ፡ አለብኝ ፡ የምስጋና
እልፍ ፡ ዕዳ ፡ አለብኝ ፡ የእልልታ/የውለታህ
እልፍ ፡ ዕዳ ፡ አለብኝ ፡ የዝማሬ
እልፍ ፡ ዕዳ ፡ አለብኝ የውዳሴ