From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation
Jump to search
|
|
ሃና ፡ ተክለ (Hana Tekle)
|
|
|
|
፬ (4)
|
መሥዋዕት (Meswaet)
|
| ዓ.ም. (Year):
|
2024
|
| ቁጥር (Track):
|
፲ ፫ (13)
|
| ርዝመት (Len.):
|
6:33
|
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች (Other Songs in the Album)
|
|
|
የሃና ፡ ተክለ ፡ አልበሞች (Albums by Hana Tekle)
|
|
|
ጨለማችንን ፡ አበራው ፡ ኢየሱስ ፡ አበራው
የእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ ዕዳችንን ፡ ከፈለው
ያታገለን ፡ የሞት ፡ ቀንበር ፡ ተሻረ
በበጉ ፡ ደም ፡ ሕይወታችን ፡ ከበረ
ከቋንቋ ፡ ከነገድ
ከሕዝብም ፡ ሁሉ ፡ ከወገን
ይኸው ፡ ዋጀን ፡ ለመንግስቱ
አደረገን ፡ ካህናቱ
ማኀተሙን ፡ ይፈታ ፡ ዘንድ ፡ ድል ፡ የነሣው
መጽሐፉን ፡ ሊዘረጋ ፡ የተቻለው
ታርዷልና ፡ ይገባዋል ፡ ብዙ ፡ ክብር
የይሁዳ ፡ ነገድ ፡ አንበሳ ፡ የዳዊት ፡ ሥር
ከቋንቋ ፡ ከነገድ
ከሕዝብም ፡ ሁሉ ፡ ከወገን
ይኸው ፡ ዋጀን ፡ ለመንግስቱ
አደረገን ፡ ካህናቱ
ደሙ ፡ ነው ፡ ሰው ፡ ያረገን
ስሙ ፡ ነው ፡ ያዳነን
ክቡር ፡ ይሁን ፡ ለስሙ
ላዳነን ፡ በደሙ
ስሙ ፡ ነው ፡ ሰው ፡ ያረገን
ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ያዳነን
ክቡር ፡ ይሁን ፡ ለስሙ
ላዳነን ፡ በደሙ
ሃሌሉያ ፡ ሃሌሉያ ፡ ክብር ፡ ክብር
ለታረደው ፡ በግ ፡ ኃይልና ፡ ባለጠግነት ፡ ክብር
ለታረደው ፡ በግ ፡ ጥበብ ፡ ብርታት ፡ በረከት -ይገባዋል
የታረደው ፡ በግ ፡ ኃይልና ፡ ባለጠግነት ፡ ክብር
የታረደው ፡ በግ ፡ ጥበብ ፡ ብርታት ፡ በረከት -ይገባዋል
ምስጋና ፡ ምስጋና ፡ ምስጋና ፡ ይገባዋል
ክብር ፡ ክብር ፡ ሊቀበል ፡ ይገባዋል
|