አየሱስ ፡ ፍቅር (Eyesus Fiker) - ሃና ፡ ተክለ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search
ሃና ፡ ተክለ
(Hana Tekle)

፬
(4)

አልበም
(Meswaet)

ዓ.ም. (Year): 2024
ቁጥር (Track):

፲ ፩ (11)

ርዝመት (Len.): 6:23
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሃና ፡ ተክለ ፡ አልበሞች
(Albums by Hana Tekle)

የማያረጅ ፡ መውደድ ፡ የማይቀያየር
ወረት ፡ የማያውቀው ፡ እውነተኛ ፡ ፍቅር
የኢየሱስ ፡ ፍቅር ፡ ነው
የማያረጅ ፡ መውደድ ፡ የማይቀያየር
ወረት ፡ የማያውቀው ፡ የሕይወት ፡ ሁሉ ፡ ሥር
የኢየሱስ ፡ ፍቅር
የጌታዬ ፡ ፍቅር

የፍቅርን ፡ ትርጉም ፡ አትፈልጉት ፡ የትም
ከኢየሱስ ፡ በስተቀር ፡ የትም ፡ አይገኝም
ነፍሱን ፡ በመስቀል ፡ ላይ ፡ ሰጠን ፡ በጭንቅ ፡ አልፎ
እንደሰው ፡ ተገኘ ፡ ክብሩን ፡ አሳልፎ
የኢየሱስ ፡ ፍቅር
የጌታዬ ፡ ፍቅር


ሐብታም ፡ ደሀ ፡ የለም ፡ ሁሉም ፡ ይወደዳል
የሚናቅ ፡ ነፍስ ፡ የለም ፡ ሁሉን ፡ ይፈልጋል
ፍቅሩ ፡ እንደባህር ፡ ነው ፡ የማይነጥፍ ፡ ዘላለም
ለሰው ፡ ልጅ ፡ በሙሉ ፡ ቢቀዳ ፡ አይጎድልም
የኢየሱስ ፡ ፍቅር
የጌታዬ ፡ ፍቅር

ማይለወጥ ፡ የማይናወጥ ፡ ፍቅር ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
ማይመዘን ፡ የማይለካ ፡ ዘላለም ፡ ውድ ፡ ነው
ማይናወጥ ፡ የማይለወጥ ፡ ፍቅር ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
ማይመዘን ፡ የማይለካ ፡ ዘላለም ፡ ሚወደው
ኢየሱስ ፡ ፍቅር ፡ ነው
ጌታዬ ፡ ፍቅር ፡ ነው

የሕይወት ፡ ምንጭ
ኢየሱስ ፡ ፍቅር