መንፈስ ፡ ቅዱስ (Menfes Kidus) - ሃና ፡ ተክለ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search
ሃና ፡ ተክለ
(Hana Tekle)

፬
(4)

መስዋዕት
(Meswaet)

ዓ.ም. (Year): 2024
ቁጥር (Track):

፰ (8)

ርዝመት (Len.): 5:50
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሃና ፡ ተክለ ፡ አልበሞች
(Albums by Hana Tekle)

አፅናኙን ፡ መንፈስ ፡ ልኮልናል ፡ በሰላሙ/በእውነቱ ፡ ይምሎናል
ምን ፡ ምሰማው ፡ ባይሆን ፡ ደህና
እንፀናለን ፡ መንፈሱ/አምላክ ፡ አለንና
እንቆማለን ፡ መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ አለንና
 
ከማዕበሉ ፡ በላይ ፡ ከወጀቡም ፡ በላይ
ከችግሩም ፡ ጥልቀት ፡ ከምንሰማው/ከምናየው ፡ በላይ
ብርቱ/ደህና ፡ የሚያረገን ፡ መንፈሱ ፡ አይደል ፡ ወይ
በጨለማው ፡ ዓለም ፡ ጨለማው ፡ በርትቷል
 የጭንቅ ፡ የምጥ ፡ ዜናው ፡ ቀን ፡ ከሌት ፡ ይፋጃል
የብርሀኑ ፡ መንፈስ ፡ ልባችንን ፡ ያዘው
አንጅማ ፡ ከፍሙ ፡ ማን ፡ ነው ፡ ምተርፈው

መንፈስ ፡ ቂዱስ ፡ ተሰቶናል ፡ በሰላሙ/በእውነቱ ፡ ይሞላናል/ይመራናል
በእውነቱ/ በሰላሙ ፡ እየመራ ፡ እስከፅዖን ፡ ያዘልቀናል/ያደርሰናል

ትናንት ፡ ዛሬም ፡ ነገም ፡ መንፈሱ ፡ ይሰራል
ለደረኩ ፡ አጥንቶች ፡ ሕይወትን ፡ ያድላል
ተስፋ ፡ ለሌላቸው ፡ ተስፋ ፡ ተገን ፡ ሆኖ
አለ ፡ መሀላችን ፡ በልባችን ፡ ገኖ

መንፈስ ፡ ቂዱስ ፡ ተሰቶናል ፡ በሰላሙ/በእውነቱ ፡ ይሞላናል/ይመራናል
በእውነቱ/ በሰላሙ ፡ እየመራ ፡ እስከፅዖን ፡ ያዘልቀናል/ያደርሰናል