በማለዳ (Bemaleda) - ሃና ፡ ተክለ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search
ሃና ፡ ተክለ
(Hana Tekle)

፬
(4)

መሥዋዕት
(Meswaet)

ዓ.ም. (Year): 2024
ቁጥር (Track):

፩ (1)

ርዝመት (Len.): 5:58
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሃና ፡ ተክለ ፡ አልበሞች
(Albums by Hana Tekle)

የተገባህ ፡ ምስጋና ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ የኔ ፡ ጌታ
የተገባህ ፡ ክብር ፡ ላንተ ፡ ነው ፡ የኔ ፡ ጌታ
በምስጋና ፡ ወደፊትህ ፡ እቀርባለሁ ፡ ላመልክህ
እግዚአብሔር ፡ አምላኬ ፡ ሆይ ፡ ይገባሃልና ፡ ለስምህ

በምስጋና ፡ የተፈራህ ፡ ገናና ፡ አምላክ ፡ ነህ
ለዑል ፡ አምላክ ፡ ብንዘምርህ ፡ ብንሰግድልህ ፡ አይበቃህም
አእላፋት ፡ ያንተ ፡ ፍጥረት ፡ ላንተ ፡ ክብር ፡ ያዜማሉ
ቀን ፡ ከለሊት ፡ ያንተን ፡ ስራ ፡ በምስጋና ፡ ያውጃሉ

በማለዳ ፡ ምስጋናዬን ፡ አበዛለሁ ፡ እኔ ፡ አበዛለሁ
በቀትርም/በሌሊትም ፡ ዝማሬዬን ፡ አበዛለሁ ፡ አበዛለሁ /x፪

ስምህ ፡ ሀያል ፡ የአማልክቱም ፡ አምላክ ፡ ገዢ ፡ ነህ
ታላቅ ፡ ጌታ ፡ የሆነልህ ፡ ሰማይ ፡ ምድሩ ፡ ምስጋናህ
መላዕክቱ ፡ ላንተ ፡ ሞገስ ፡ ላንተ ፡ ግርማ ፡ ይዘምራሉ
ባይገልፅህም ፡ በአዲስ ፡ ቅኔ ፡ ምስጋናህን ፡ ያውዳሉ

በማለዳ ፡ ምስጋናዬን ፡ አበዛለሁ ፡ እኔ ፡ አበዛለሁ
በቀትርም/በሌሊትም ፡ ዝማሬዬን ፡ አበዛለሁ ፡ አበዛለሁ /x፪

ለኔ ፡ ብዙ ፡ ተደርጎልኛል/ሆኖልኛል ፡ ኧረ ፡ አኔ ፡ ብዙ ፡ ሆኖልኛል/ተደርጎልኛል
ከማመስገን ፡ በቀር ፡ ምን ፡ ይሻለኛል
ከማመስገን ፡ በቀር ፡ ምን ፡ ይገልፅልኛል
ከማመስገን ፡ በቀር ፡ ምን ፡ ይበጀኛል
ከማመስገን ፡ በቀር ፡ ምን ፡ ይገልፅልኛል /x፪

እስትንፋስ ፡ ያለው ፡ ሁሉ ፡ እግዚአብሔርን ፡ ያመስግን
እግዚአብሔርን ፡ ያመስግን /x፬