አግዚአብሔር (Egziabeher) - ሃና ፡ ተክለ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search
ሃና ፡ ተክለ
(Hana Tekle)

፬
(4)

መሥዋዕት
(Meswaet)

ዓ.ም. (Year): 2024
ቁጥር (Track):

፲ ፬ (14)

ርዝመት (Len.): 5:37
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሃና ፡ ተክለ ፡ አልበሞች
(Albums by Hana Tekle)

በሰማይ ፡ በምድር ፡ አቻ ፡ የለህ
ወሰን ፡ ልኬት ፡ የለው ፡ ግዛትህ
ክብርህ ፡ ሰማያትን ፡ ሸፍኖ
ላይደረስበት ፡ አለ ፡ ገኖ
እግዚአብሔር ፡ እግዚአብሔር

አንተ ፡ ሰማያትን ፡ ምድርን ፡ ሞልተሀል
አለቅነት ፡ ስልጣን ፡ አንተን ፡ ያመልኩሀል
የለም ፡ ካንተ ፡ በላይ ደርሶ ፡ ሚጠጋጋ
ገናናነት ፡ ክብር ፡ ሁሌም ፡ አንተ ፡ ጋ
እግዚአብሔር ፡ እግዚአብሔር

ሁሉን ፡ ታደርግ ፡ ዘንድ ፡ ቻይ ፡ ነህ ፡ አንተ
ሀሳብህም ፡ ከቶ ፡ አይከለከልም
በምድር ፡ ያለው ፡ ሁሉ ፡ ገንዘብህ ፡ ነው
ካንተ ፡ የተሰወረ ፡ የለም ፡ ምንም
እግዚአብሔር ፡ እግዚአብሔር

ከዜማ ፡ በላይ ፡ ነው ፡ ክብርህ
ከቃላት ፡ በላይ ፡ ነው ፡ ማንነትህ
እግዚአብሔር ፡ አንተ ፡ ታላቅ ፡ ነህ
አንተን ፡ መሣይ ፡ የሌለህ
እግዚአብሔር ፡ እግዚአብሔር