እግዚአብሔር (Egziabher) - ሀና ፡ ተክሌ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search
ሀና ፡ ተክሌ
(Hana Tekle)

፬
(4)

መሥዋዕት
(መሥዋዕት)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፲ ፬ (2024)
ቁጥር (Track):

፲ ፬ (14)

ርዝመት (Len.): 5:36
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሀና ፡ ተክሌ ፡ አልበሞች
(Albums by Hana Tekle)

በሰማይ በምድር አቻ የለህ
ወሰን ልኬት የለው ግዛትህ
ክብርህ ሰማያትን ሸፍኖ
ላይደረስበት አለ ገኖ

ሰማይ በምድር አቻ የለህ
ወሰን ልኬት የለው ግዛትህ
ክብርህ ሰማያትን ሸፍኖ
አይደረስበትም አለ ገኖ

እግዚአብሔር እግዚአብሔር 4x

አንተ ሰማያትን ምድርን ሞልተሀል
አለቅነት ስልጣን አንተን ያመልኩሀል
የለም ካንተ በላይ ደርሶ ሚጠጋጋ
ገናናነት ክብር ሁሌም አንተ ጋ

እግዚአብሔር እግዚአብሔር 4x

ሁሉን ታደርግ ዘንድ ቻይ ነህ አንተ
ሀሳብህም ከቶ አይከለከልም
በምድር ያለው ሁሉ ገንዘብህ ነው
ካንተ የተሰወረ የለም ምንም

እግዚአብሔር እግዚአብሔር 4x


ከዜማ በላይ ነው ክብርህ
ከቃላት በላይ ነው ማንነትህ
እግዚአብሔር አንተ ታላቅ ነህ
አንተን መሣይ የሌለህ።።።። 2x

እግዚአብሔር እግዚአብሔር 4x