ኃይሌም (Hailem) - ሃና ፡ ተክለ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search
ሃና ፡ ተክለ
(Hana Tekle)

፬
(4)

መሥዋዕት
(Meswaet)

ዓ.ም. (Year): 2024
ቁጥር (Track):

፲ (10)

ርዝመት (Len.): 5:02
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሃና ፡ ተክለ ፡ አልበሞች
(Albums by Hana Tekle)

በ"ይሁን!"ብቻ ፡ በቃልህ ፡ ብቻ ፡ ሰማይ ፡ ምድሩ ፡ ቀና
የስምህ ፡ ጉልበት የኃይልህ ፡ ችሎት ፡ ሁሉን ፡ አፀና
የሰው ፡ ክንድ ፡ የአንተን ፡ አይቋቋምም ፡ ከቶ ፡ ችሎ
አትገመትም ፡ አትጨረስም ፡ እንዲህ ፡ ነህ ፡ ተብሎ

ምን ፡ ቢሰበሰብ ፡ ኃይል
ቢመስል ፡ ሲታይ ፡ የሚያይል
አንተን ፡ ያመነህ ፡ ግን ፡ አይወድቅም
ካንተ ፡ ማንም ፡ አይቀድምም
የምድሩ ፡ ኃይል ፡ ተጠቅጥቆ
ቢያሰፈስፍ ፡ ሊታይ ፡ ልቆ
የፈጠርከው ፡ አይገዛህም!
ኃይል ፡ ያንተ ፡ ነው ፡ አይቻልም!

በስብርባሪ ፡ ደህና ፡ የደረሰ ፡ አለ ፡ ባንተ ፡ ጉልበት
ደሞም ፡ በጠጠር ኃያሉን ፡ ጥለህ ፡ አየን ፡ እንደዘበት
አበቃ ፡ ሲባል ፡ ያንተ ፡ ይጀምራል ፡ ያለገደብ
ከልካይ ፡ የለህም! ካሰብክ ፡ ልትሰራ ፡ አትወሰንም!

ምን ፡ ቢሰበሰብ ፡ ኃይል
ቢመስል ፡ ሲታይ ፡ የሚያይል
አንተን ፡ ያመነ ፡ ግን ፡ አይወድቅም
ካንተ ፡ ማንም ፡ አይበልጥም
የምድሩ ፡ ኃይል ፡ ተጠቅጥቆ
ቢያሰፈስፍ ፡ ሊታይ ፡ ልቆ
የፈጠርከው ፡ አይቀድምህም!
ካንተ ፡ ማንም ፡ አይበልጥም!

የኔ ፡ ኃይል ፡ ጥቂት ፡ ትንሽ ፡ ቢሆንም
የዙሪያዬ ፡ ድምፅ ፡ ጉልበት ፡ ቢያይልም
ያመንኩትን ፡ ክንድ ፡ ግን ፡ የለም ፡ ሚያክለው
አልናወጥም ፡ ኃይል ፡ የእግዚአብሔር ፡ ነው
እርሱ ፡ የዘጋውን ፡ የሚከፍት ፡ የለም
የለም ፡ ሚዘጋ ፡ የከፈተውንም
ብርቱ ፡ ክንድ ፡ አለው ፡ የማይለካ
የታመኑትን ፡ የማያስነካ
ብርቱ ፡ ክንድ ፡ አለው ፡ የማይነካ
የታመኑትን ፡ የማያስነካ

ረዳቴ ፡ ሰማይና ፡ ምድርን ፡ ከፈጠረ
ከእግዚአብሔር ፡ ዘንድ ፡ ነው
የኔ ፡ ጉልበት ፡ ሰማይና ፡ ምድርን ፡ ከፈጠረ
ከእግዚአብሔር ፡ ዘንድ ፡ ነው
ኃይሌም ፡ ዝማሬዬም ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው!
ኃይሌም ፡ ዝማሬዬም ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው!
ኃይሌም ፡ ዝማሬዬም ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው!
ኃይሌም ፡ ዝማሬዬም ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው!