ቆጠርቀኝ (Koterkegn) - ሃና ፡ ተክለ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search
ሃና ፡ ተክለ
(Hana Tekle)

፬
(4)

መሥዋዕት
(Meswaet)

ዓ.ም. (Year): 2024
ቁጥር (Track):

፲ ፪ (12)

ርዝመት (Len.): 6:39
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሃና ፡ ተክለ ፡ አልበሞች
(Albums by Hana Tekle)

የዓለምን ፡ ጥበብ ፡ ልታሳፍር ፡ ሞኝን ፡ ነገር ፡ የመረጥህ
ብርቱውንም ፡ ደግሞ ፡ ልታሳፍር ፡ ደካማውን ፡ የፈለግህ
ይደንቀኛል ፡ አደራረግህ-የኔን ፡ ሕይወት ፡ እንዲህ ፡ አደረግህ
ይገርመኛል ፡ አሰራርህ- የኔን ፡ ህይወት ፡ እንዲህ ፡ ያደረግህ

ቆጠርከኝ ፡ ታማኝ ፡ አድርገህ
የሾምከኝ ፡ ለቤትህ ፡ አምነህ
ምን ፡ አይነት ፡ ፍቅር ፡ ነው ፡ ያንተስ
ሰው ፡ ሰውን ፡ እንደሚያይ ፡ መቼ ፡ ታያለህ
የቆጠርከኝ ፡ ታማኝ ፡ አድርገህ
የሾምከኝ ፡ ለቤትህ ፡ አምነህ
ምን ፡ አይነት ፡ አምላክ ፡ ነህ ፡ አንተስ
ሰው ፡ ሰውን ፡ እንደሚያይ ፡ መቼ ፡ ታያለህ

አይቸግርህም ፡ አንተን ፡ የሰው ፡ ብዛት
የሚያመልክህ ፡ በብዙ ፡ ትጋት
እኔን ፡ ደካማዋን ፡ ለየህ ፡ ለክብርህ
በፊትህ ፡ ልቆም ፡ ላጥን ፡ በቤትህ
እኔን ፡ ደካማዋን ፡ ለየህ ፡ ለክብርህ
በፊትህ ፡ ልቆም ፡ ላጥን ፡ በቤትህ

ቆጠርከኝ ፡ ታማኝ ፡ አድርገህ
የሾምከኝ ፡ ለቤትህ ፡ አምነህ
ምን ፡ አይነት ፡ ፍቅር ፡ ነው ፡ ያንተስ
ሰው ፡ ሰውን ፡ እንደሚያይ ፡ መቼ ፡ ታያለህ
የቆጠርከኝ ፡ ታማኝ ፡ አድርገህ
የሾምከኝ ፡ ለቤትህ ፡ አምነህ
ምን ፡ አይነት ፡ አምላክ ፡ ነህ ፡ አንተስ
ሰው ፡ ሰውን ፡ እንደሚያይ ፡ መቼ ፡ ታያለህ

በአይኖችህ ፡ ታየሁኝ ፡ አገኘኝ ፡ ሞገስህ
የማልበቃውን ፡ ሰው ፡ ብቁ ፡ አረገኝ ፡ ጥበብህ
ይኸው ፡ ዝማሬ ፡ ላንተ ፡ ምስጋና
ያበጃጀኸኝ ፡ አንተ ፡ ነህና
ይኸው ፡ ክብር ፡ ይሁን ፡ ምስጋና
ለክብር ፡ ያረግከኝ ፡ አንተ ፡ ነህና

ቆጠርከኝ ፡ ታማኝ ፡ አድርገህ
የሾምከኝ ፡ ለቤትህ ፡ አምነህ
ምን ፡ አይነት ፡ ፍቅር ፡ ነው ፡ ያንተስ
ሰው ፡ ሰውን ፡ እንደሚያይ ፡ መቼ ፡ ታያለህ
የቆጠርከኝ ፡ ታማኝ ፡ አድርገህ
የሾምከኝ ፡ ለቤትህ ፡ አምነህ
ምን ፡ አይነት ፡ አምላክ ፡ ነህ ፡ አንተስ
ሰው ፡ ሰውን ፡ እንደሚያይ ፡ መቼ ፡ ታያለህ

ስምህን ፡ የሚጠሩትን ፡ ያንተን ፡ ክፉ ፡ አሳዳጅ
በደማስቆ ፡ አግኝተህ ፡ አደረግከው ፡ ሳውልን ፡ ወዳጅ
የተመረጠ ፡ የክብር ፡ እቃ
ይኸው ፡ አረግከው ፡ ለክብር ፡ በቃ
ስምህን ፡ የሚሸከም ፡ የክብር ፡ እቃ
ይኸው ፡ አረግከው ፡ ለቤትህ ፡ በቃ

የዓለምን ፡ ጥበብ ፡ ልታሳፍር ፡ ሞኝን ፡ ነገር ፡ የመረጥህ
ብርቱውንም ፡ ደግሞ ፡ ልታሳፍር ፡ ደካማውን ፡ የፈለግህ
ይደንቀኛል ፡ አደራረግህ-የኔን ፡ ሕይወት ፡ እንዲ ፡ አደረግህ
ይገርመኛል ፡ አሰራርህ- የኔን ፡ ህይወት ፡ እንዲህ ፡ ያደረግህ

ቆጠርከኝ ፡ ታማኝ ፡ አድርገህ
የሾምከኝ ፡ ለቤትህ ፡ አምነህ
ምን ፡ አይነት ፡ ፍቅር ፡ ነው ፡ ያንተስ
ሰው ፡ ሰውን ፡ እንደሚያይ ፡ መቼ ፡ ታያለህ
የቆጠርከኝ ፡ ታማኝ ፡ አድርገህ
የሾምከኝ ፡ ለቤትህ ፡ አምነህ
ምን ፡ አይነት ፡ አምላክ ፡ ነህ ፡ አንተስ
ሰው ፡ ሰውን ፡ እንደሚያይ ፡ መቼ ፡ ታያለህ