አሐዱ ፡ አምላክ (Ahadu Amlak) - ሐምሌት ፡ በልጁን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search
ሐምሌት ፡ በልጁን
(Hamlet Beljun)

፪
(2)

የለሁበትም
(Yelehubetm)

ዓ.ም. (Year): 2025
ቁጥር (Track):

፩ (1)

ርዝመት (Len.): 6:14
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሐምሌት ፡ በልጁን ፡ አልበሞች
(Albums by Hamlet Beljun)

ማንስ ፡ በአይንህ ፡ ፊት ፡ ገዝፎ ፡ ተልቆብህ
ማንን 'አንቱ' ብለህ ፡ ትጠራዋህ?
ተራሮች ፡ ሳይወለዱ ፡ አለማት ፡ ሳይዋቀሩ
ከዘላለም ፡ በፊት ፡ የነበርክ ፡ ህያው ፡ አሀዱ ፡ አምላክ

ያለ ፡ የሚኖር ፡ ማንነትህ
ሁሉ ፡ ንብረትህ ፡ ነው ፡ ግዛትህ
ፍጥረት ፡ በፊትህ ፡ ሚንቀጠቀጥ
እንኳን ፡ የሰው ፡ ልጅ ፡ ግዑዝ ፡ ሚቀልጥ

ብትመሰገን ፡ ስለሌለህ ፡ እንከን
ብትወደስ ፡ ነህና ፡ ንጉስ
ብናመልክህ ፡ ጠፍቶ ፡ ሚመስልህ
አልፋ ፡ ኦሜጋ ፡ መጠሪያ ፡ ስምህ

ቃልህ ፡ አይታጠፍ ፡ ያልከው ፡ አያልፍ
ተሳስተህ ፡ አታውቅም ፡ አትታረምም
ካለመኖር ፡ መቷል ፡ ሁሉን ፡ ይሁን ፡ ስትል
እንኳንስ ፡ አንተ ፡ ስራህ ፡ ከአዕምሮ ፡ ያልፋል

ለከዋክብቱ ፡ ሰጠህ ፡ መጠሪያ
ለቀን ፡ ጨለማ ፡ መሰማሪያ
ሁሉን ፡ ደግፈህ ፡ በስልጣን ፡ ቃል
አለማት ፡ ፀኑ ፡ በማስተዋልህ
 
አቻ ፡ ቢሆን ፡ እኩያ ፡ የለህም ፡ መንትያ
በሰማይ ፡ በምድር ፡ አልተገኘልህ ፡ ወደር

ብትመሰገን ፡ ስለሌለህ ፡ እንከን
ብትወደስ ፡ ነህና ፡ ንጉስ
ብናመልክህ ፡ ጠፍቶ ፡ ሚመስልህ
አልፋ ፡ ኦሜጋ ፡ መጠሪያ ፡ ስምህ

ፍጥረት ፡ ከበታች ፡ ሚያይህ ፡ ወደላይ
ባንተ ፡ ባምላኩ ፡ በተስፋ ፡ ያድራል
እስትንፋስህን ፡ ብትሰበስበው
ስጋ ፡ ለባሽ ፡ ሁሉ ፡ አፈር ፡ ነው

አህዛብ ፡ በገንቦ ፡ እንዳለች ፡ ጠብታ
በአንተ ፡ ሚዛን ፡ የታዪ ፡ ለታ
በማንም ፡ ግንባር ፡ ልብህ ፡ አይሸበር
ጉልበት ፡ ይገዛል ፡ ለአንተ ፡ ክብር

አቻ ፡ ቢሆን ፡ እኩያ ፡ የለህም ፡ መንትያ
በሰማይ ፡ በምድር ፡ አልተገኘልህ ፡ ወደር

ብትመሰገን ፡ ስለሌለህ ፡ እንከን
ብትወደስ ፡ ነህና ፡ ንጉስ
ብናመልክህ ፡ ጠፍቶ ፡ ሚመስልህ
አልፋ ፡ ኦሜጋ ፡ መጠሪያ ፡ ስምህ