የማይታይ ፡ አምላክ ፡ ምሳሌ፣
የአብ ፡ ማንነቱ ፡ ትንታኔ፣
ከፍጥረታት ፡ በፊት ነህ ፡ አልፋ፣
ሁሉ ፡ በአንተ ፡ ላንተ ፡ ነህ ፡ ዖሜጋ።
አትመረመር ፡ ኢየሱስ ፡ ረቂቅ ፡ ነህ፤
ማን ፡ ያውቀዋል ፡ መንገድህን?
አትመረመር ፡ ኢየሱስ ፡ ረቂቅ ፡ ነህ፤
ከ ፡ እስከ ፡ የለው ፡ ዕድሜ ፡ ዙፋንህ!
ሳትመጣ ፡ ወደ ፡ ምድር ፡ ቃል ፡ ሥጋ ፡ ሆነህ፣
‘ምትመለክ ፡ በመንበርህ፣
ሳትታቀፍ ፡ በፊት ፡ በሰው ፡ እጅ ፡ ወርደህ፣
ዘላለማዊ ፡ ጅማሬ ፡ የሌለህ።
ጎንህ ፡ ሳይወጋ ፡ ታዘህ ፡ ለመስቀል፣
ሁን ፡ ብለኸው ፡ ፍጥረት ፡ ተጋጥሟል፤
ሳታስታርቅ ፡ በሞት ፡ ሰማይን ፡ ከምድር፣
ክርስቶስ ፡ ኢየሱስ ፡ አንተ ፡ ወልድ ፡ እግዚአብሔር።
አትመረመር ፡ ኢየሱስ ፡ ረቂቅ ፡ ነህ፤
ማን ፡ ያውቀዋል ፡ መንገድህን?
አትመረመር ፡ ኢየሱስ ፡ ረቂቅ ፡ ነህ፤
ከ ፡ እስከ ፡ የለው ፡ ዕድሜ ፡ ዙፋንህ!
ላለውና ፡ ለነበረው ፡ ለሚመጣው፣
ሁሉንም ፡ ጠቅልሎ ፡ ለሚገዛው፣
አለቅነት ፡ ሥልጣናት፣
ፍጥረት ፡ ሁሉ ፡ ይሰግዳል፤
ለእርሱ ፡ ጌትነት! (*2)