እጠብቅለሁ (Etebkhalew) - ሐምሌት ፡ በልጁን

ሐምሌት ፡ በልጁን
(Hamlet Beljun)

፪
(2)

የለሁበትም
(Yelehubetm)

ዓ.ም. (Year): 2025
ቁጥር (Track):

፲ ፫ (13)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሐምሌት ፡ በልጁን ፡ አልበሞች
(Albums by Hamlet Beljun)

የሙጥኝ ፡ ብዬ ፡ ናልኝ ፡ ባልኩህ ፡ ጉዳይ፣
 “በስፍራሽ ፡ ጠብቂኝ ፡ እመጣለሁ” ባልከኝ፥
እኔ ፡ ያሰመርኩት ፡ የቆረጥሁት ፡ ቀን ፡ ቢያልፍ፣
ስፍራዬን ፡ ለቅቄ ፡ እንዳንተላለፍ፣
ትናንት ፡ ያ’ረግኸውን ፡ ታማኝነትህን፣
እጠብቃለሁ ፡ አስቤ ፡ እውነትህን፣
ታግሼ ፡ እውነትህን።

እጠብቅሀለሁ ፡ በስፍራዬ፣ እስክትመጣ ፡ ጌታዬ፣
እጠብቅሀለሁ ፡ ሳልላወስ፣ ጊዜህን ፡ በመታገሥ።

“ዘርህን ፡ አበዛለሁ ፡ እንደ ፡ ሰማይ ፡ ከዋክብት፣
ተብለህ ፡ ትጠራለህ ፡ የአሕዛብ ፡ ሁሉ ፡ አባት”
ያልከው ፡ ቃል ፡ ቢዘገይ እስኪመስል ፡ የተረሳ፣
ወደ ፡ አጋር ፡ ገባ ፡ በእስማኤል ፡ ሊወሳ፣
ተስፋውን ፡ ሊጨብጥ ፡ በገዛ ፡ መንገዱ፣
ይስሐቅን ፡ ለማቀፍ ፡ ባቋራጭ ፡ ቢሄዱ፣
ከባሪያዪቱ ፡ አይደል ፡ የቃልኪዳን ፡ ልጅ፣
እግዚአብሔር ፡ ካየው ፡ ከነጻዪቱ ፡ እንጂ።
በሰው ፡ ቀመር ፡ አይደል ፡ ምትመጣ ፡ ያንተ ፡ እጅ
አንተ ፡ በወደድከው ፡ ባንተው ፡ ሰዓት ፡ እንጂ

እንድጠብቅ ፡ ነቅቼ ፡ ተዘጋጅቼ፣
እንዳያዝንብኝ ፡ ልቤ ፡ እምነቴን ፡ አንግቤ፣
ጸጋህ ፡ ይርዳኝ ፡ እንድጸና ፡ እኔ ፡ የድርሻዬን፣
ሰማይ ፡ ምድር ፡ ቢያልፉ ፡ ይቀልላል፣
አንተማ ፡ ከምታጥፍ ፡ ቃልህን።

እግዚአብሔር ፡ ቃሉን ፡ አያጥፍም፤
ይዋሽ ፡ ዘንድ ፡ ሰው ፡ አይደለም፤
ይመጣል ፡ እመጣለሁ ፡ ካለ፣
ዙሪያዬ ፡ ቢለኝ “የታለ?”
የተሰወርሁ ፡ አይደለሁም ፡ ከዐይኑ፣
አላለፈም ፡ የፍርዴም ፡ ሚዛኑ፣
በከንቱ ፡ አይደል ፡ ጥበቃዬ፣
ሁሉን ፡ መልካም ፡ ያደርጋል ፡ ጌታዬ።
ነገዬን ፡ ሳቅ ፡ ያደርጋል ፡ ጌታዬ።

እጠብቅሀለሁ ፡ በምስጋና ፡ ትመጣለህና፣
እጠብቅሀለሁ ፡ በደስታ ፡ ታማኝ ፡ የኔ ፡ ጌታ፤