ዘላለም (Zelalem) - ሐምሌት ፡ በልጁን

ሐምሌት ፡ በልጁን
(Hamlet Beljun)

፪
(2)

የለሁበትም
(Yelehubetm)

ዓ.ም. (Year): 2025
ቁጥር (Track):

፯ (7)

ርዝመት (Len.): 5:55
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሐምሌት ፡ በልጁን ፡ አልበሞች
(Albums by Hamlet Beljun)

እኔ ፡ ምን ፡ ሕይወት ፡ አለኝ? ከሰጠኸኝ ፡ ሌላ?አሃ
እኔ ፡ ምን ፡ ታሪክ ፡ አለኝ? ከሆንህልኝ ፡ ሌላ?
እኔ ፡ ምን ፡ ትምክህት ፡ አለኝ? ከመስቀልህ ፡ ሌላ! አሃ
ካንተ ፡ ውጭ ፡ ምን ፡ ተስፋ ፡ አለኝ? ከእንግዲህ ፡ በኋላ!

ታሪኬን ፡ ለመንገር ፡ ብጀምር፣
ምን ፡ አለ ፡ ምሕረትህ ፡ ከጻፈው ፡ በቀር ፡ የሚነገር፣
ቀለም ፡ አልባ ፡ ሕይወቴን ፡ ይቅርታህ ፡ አቅልሞ፣
ሰማያዊ ፡ አ’ረገው ፡ በደም ፡ አትሞ፣
ጣዕም ፡ አልባ ፡ ሕይወቴን ፡ ፍቅርህ ፡ ቀምሞ፣
ጣፋጭ ፡ አደረገው ፡ የሚተርፍ ፡ ደሞ።

ያለሁት ፡ በምሕረትህ፣ የሚያኖረኝ ፡ ችሮታህ፣
ይሄ ፡ ነው ፡ ታሪኬ ፡ ይመሰገን ፡ ስምህ፤
ሽረኸው ፡ ባርነቴን፣ ዐወጅኸው ፡ ነጻነቴን፣
ይሄ ፡ ነው ፡ ታሪኬ ፡ ይመሰገን ፡ ስምህ።

ስርዝ ፡ ድልዝ ፡ ነበር ፡ የተሞነጫጨረው፣
ጨለማዬን ፡ ገፍፈህ ፡ በብርሃን ፡ እስክትጽፈው፣ ስታትመው ፡ ስሜን ፡ በዘላለም ፡ መዝገብ፣
ያን ፡ ጊዜ ፡ ታሪኬ ፡ ጀመረ ፡ መነበብ።

ያለሁት ፡ በምሕረትህ፣ የሚያኖረኝ ፡ ችሮታህ፣
ይሄ ፡ ነው ፡ ታሪኬ ፡ ይመስገን ፡ ስምህ፤
አስዋብከው ፡ አድራሻዬን፣ ቀይረህ ፡ ፍለጋዬን፣
ይሄ ፡ ነው ፡ ታሪኬ ፡ ይመስገን ፡ ስምህ።

ከእንግዲህ ፡ ምኖረው ፡ የእኔ ፡ ሕይወት፣
በእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ ላይ ፡ ባለኝ ፡ እምነት፣
ለወደደኝ ፡ ራሱን ፡ ለሰጠኝ፣
ለዓለም ፡ ሞቼ ፡ ለእ’ሱ ፡ ሕያው ፡ ነኝ።

ኢየሱስ (*6) የኔ ፡ ታሪክ ፡ የኔ ፡ ሕይወት