አንደበት ፡ እሳትን ፡ ነው ፡ በጉያው ፡ ያቀፈው፣
‘ሚገድል ፡ እሚያድን ፡ ፍጹም ፡ ኀይል ፡ ያለው፤
ሞትና ፡ ሕይወት ፡ በምላስ ፡ እጅ
ሁለት ፡ ጽንፍ ፡ ፍሬ፣ ጽድቅ ፡ ወይ ፡ ኩነኔ
ከዚህችው ፡ አንድ ፡ እኔ።
በዚያች ፡ ሰማሪያ ፡ ጽኑ ፡ ረሀብ ፡ ገብቶ፣
“ነገ ፡ ጥጋብ ፡ ነው” ቢል ፡ ባሪያው ፡ ከአምላኩ ፡ ሰምቶ፣
“ይህ ፡ እንዴት ፡ ይሆናል ፡ ቢከፋፈት ፡ ሰማይ?
የችግሩ ፡ ጥልቀት ፡ የሚታይ ፡ አይደል ፡ ወይ?”
የንጉሥ ፡ ጥበቃ ፡ በእምነት ፡ ቃል ፡ ዘበተ፤
የልቡ ፡ ስንፍና ፡ አፉን ፡ አስከፈተ።
እ’ሱ ፡ ብቻ ፡ ነው ፡ ወይ ፡ ያላመነው ፡ ከሁሉ፣
ጥፋት ፡ ደጁን ፡ ማሰ፤ አንደበቱን ፡ ባለመከልከሉ፤
ምርኮን ፡ አይቶ ፡ ሳይቀምስ ፡ ተረጋግጦ ፡ ሞተ
ምን ፡ ነበር ፡ ዝም ፡ ቢል? ባፉ ፡ ባልዘመተ?
ባልገባኝ ፡ ነገር ፡ ላይ ፡ ዝም ፡ እላለሁ፤
አንደበቴን ፡ ከፍርድ ፡ እከለክላለሁ፤
ነፍሴ ፡ እንዳትዋጥ ፡ በመከራ
ሕግህ ፡ ዘወትር ፡ እኔነቴን ፡ ይግራ።
አንደበቱን ፡ የሚጠብቅ፣
ንግግሩን ፡ የሚያርቅ፣
ከተማን ፡ ከሚመራ፣
ይበልጣል ፡ መንፈሱን ‘ሚገራ።
ዘመን ፡ አይቶ ፡ አስተዋይ ፡ ዝም ፡ ይላል፤
ከፍርድ ፡ መንበር ፡ እራሱን ፡ ይገታል፤
ለሁሉ ፡ ጊዜ ፡ እንዳለው ፡ አውቆ፣
ይኖራል ፡ ሚዛኑን ፡ ጠብቆ።
የሰው ፡ ቁጣ ፡ ላይሠራ ፡ የአምላክ ፡ ጽድቅ፣
ሥጋ ፡ ለባሽ ፡ ለራስ ፡ ፍርድ ፡ አይታጠቅ፣
የእውነት ፡ ዳኛ ፡ አለ ፡ በዙፋኑ፣
በፍርድ ፡ ያልፋል ፡ በጊዜ ፡ ሚዛኑ፣
አያደላ ፡ ብያኔው ፡ የእውነት፣
በጽድቅ ፡ ነው ፡ የእርሱ ፡ ዳኝነት።
ቃል ፡ እንደ ፡ ሰይፍ ፡ ነው፤ ጠልቆ ፡ ልብ ፡ ይወጋል፤
የአንደበት ፡ ቁስል ፡ ፈጥኖ ፡ መች ፡ ይጠግጋል ?
በልብ ፡ ሀሳብ ፡ ሞልቶ ፡ በአንደበት ፡ ጎርፎ፣
ሩጫ ፡ ሳይቃጠል ፡ ጽድቅ ፡ እንነጋገር።
ዝም ፡ እላለሁ ፡ ለሁሉ ፡ ጊዜ ፡ አለው፤
ከፍርድ ፡ መንበር ፡ ምላሴን ፡ እገታለሁ።