ጉዳዬን ፡ ይዤ ፡ ስንበረከክ
ብዬ (እንደ ፡ ፈቃድህ)*2
ገና ፡ ጉልበቴ ፡ ደጅ ፡ ሳይጠና
የልቤ ፡ ሀሳብ ፡ በፊትህ ፡ ይቅና።
ለምን ፡ መልሴን ፡ ናፈቅሁ? ለምን ፡ መቀበል?
ለምን ፡ የሙጥኝ ፡ አልሁ? ለምን ፡ መታገል?
መርምር ፡ ፍላጎቴን ፡ የውስጤን ፡ መሻት፣
ታውቀዋለህና ፡ የልቤን ፡ እውነት።
የነፍሴ ፡ ንግግር ፡ የሚገባህ ፡ አንተ፣
ስንት ፡ ጸሎቴን ፡ መለስህ? እርማትን ፡ ሰጥተህ፤
እኔ ፡ እንኳን ፡ ያልገባኝ ፡ የውስጥ ፡ መሻቴ
ላንተ ፡ ጠርቶ ፡ ይታያል ፡ ግልጽ ፡ ነው ፡ አባቴ
ዐሥር ፡ ነበሩ ፡ አብዝተው ፡ የጮኹ፣
ፈውስ ፡ ፍለጋ ፡ የተማጠኑ፣
ምሕረት ፡ አግንነህ ፡ ብትለመናቸው፣
መልሳቸው ፡ ዘጠኙን ፡ ካንተ ፡ አራቃቸው።
ከማይመልሰኝ ፡ ከእግርህ ፡ ሥር
ደጅ ፡ ከሚያስቀር ፡ ከሚያባዝን
የቱም ፡ መሻቴን ፡ ሳትሰጠኝ ፡ ያዘው
ከመልሴ ፡ ይልቅ ‘ምሻው ፡ አንተን ፡ ነው።
በጎ ፡ መልካም ፡ ፈቃድህ፣ ይሁን ፡ በኔ ‘ሚያከብርህ
ይህን ፡ ብቻ ‘ፈልጋለሁ ፡ ይሁን ፡ ያልከውን ፡ አሜን ፡ እላለሁ
መና ፡ አብልተህ ፡ ሥጋ ፡ ብለው ፡ የጮኹት
ጽኑ ፡ ልቅሶአቸው ፡ ውስጥ ፡ እጅህን ፡ ነው ፡ የናቁት
ስለ ፡ ንዝነዛቸው ፡ መሻታቸውን ፡ ሞላህ
ተቆጥተሃቸው ፡ አምጣ ፡ ያሉህን ፡ ሰጠህ
ገና ፡ ሳይወርድ ፡ ከጉሮሯቸው
ስንቶች ፡ አለቁ ፡ በገዛ ፡ አምሮታቸው!
ፈቃድህ ፡ ካልሆነው ፡ ከሚያጠፋኝ ፡ መሻት
ልቤ ፡ አያዘንብል ፡ ነፍሴ ፡ አትጎራበት።
ስንት ፡ ጸሎት ፡ አለ ፡ ጸሎት ‘ሚያስፈልገው!
ስንት ፡ መሻት ፡ አለ ፡ ልጓምን ፡ የሚያሻው
ያዘው ፡ ያዘው ‘ማያከብርህን ፡ ምላሼን ፡ ያዘው።
መሻቴን ፡ ሞልተህ ፡ ከምትሄድብኝ፤
ሁሉም ፡ ይቅርብኝ ፡ ያዘው።
ያዘው ፡ ያዘው ፡ ከሕይወት ፡ ከምጎ’ል
ካንተ ፡ ከምለይ ፡ ምላሼን ፡ ያዘው፤
በጄ ፡ አይግባ ፡ ካንተ ፡ ልስማማ፤
ሁሉም ፡ ይቅርብኝ ፡ ያዘው።