ክብሬ ፡ ሆይ (Kibre Hoy) - ሐምሌት ፡ በልጁን

ሐምሌት ፡ በልጁን
(Hamlet Beljun)

፪
(2)

የለሁበትም
(Yelehubetm)

ዓ.ም. (Year): 2025
ቁጥር (Track):

፬ (4)

ርዝመት (Len.): 5:58
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሐምሌት ፡ በልጁን ፡ አልበሞች
(Albums by Hamlet Beljun)

ይበቃኝ ፡ ነበረ ፡ ቃልም ፡ ብታወጣ
ከጣርራዬም ፡ በታች ፡ ወደኔም ፡ ባትመጣ
ልትወዳጅ ፡ ከኔ ፡ ሁኔታዬን ፡ አልፈህ
ያልበቃው ፡ ሂወቴን ፡ አንተን ፡ ሳያግድህ
ደርሰህ ፡ በኔ ፡ ቅጥር ፡ በራፌን ፡ ከመታህ
እከፍታለው ፡ ጌታ

ከፍቻለው ፡ በራፌን
ላስገባ ፡ ንጉሴን
አትቁም ፡ ከደጄ
እባክህ ፡ ግባ ፡ ወዳጄ

ከልፍኜ ፡ ስትዘልቅ ፡ በራ ፡ ጨለማዬ
መዳን ፡ ለኔ ፡ ሆነ ፡ ጸናልኝ ፡ ካስማዬ
ሰላም ፡ ቤቴን ፡ ሞላው ፡ ደስታ ፡ ሆነኝ ፡ ዘመድ
ፈለቀ ፡ ከሆኔ ፡ አሃ ፡ የሂወት ፡ ውሃ ፡ ወንዝ

ክብሬ ፡ ሆይ ፡ ከእግርህ ፡ ስር ፡ እሆናለው
በልቤ ፡ ላይ ፡ በቤቴም ፡ ሾሜሀለው
የማይነጥፍ ፡ የሂወት ፡ ውሀ ፡ ምንጭ
ጌታ ፡ እየሱስ ፡ አንተ ፡ የእግዚአብሄር ፡ ልጅ
ክብሬ ፡ ሆይ ፡ ከእግርህ ፡ ስር ፡ እሆናለው
ካንተ ፡ ወዴት ፡ ወደማን ፡ እንሄዳለው
የማይነጥፍ ፡ የሂወት ፡ ውሀ ፡ ምንጭ
ጌታ ፡ እየሱስ ፡ የለም ፡ ከአንተ ፡ ውጪ


ይበቃኝ ፡ ነበረ ፡ ቃልም ፡ ብታወጣ
ከጣርራዬም ፡ በታች ፡ ወደኔም ፡ ባትመጣ
ልትወዳች ፡ ከኔ ፡ ሁኔታዬን ፡ አልፈህ
ያልበቃው ፡ ሂወቴን ፡ አንተን ፡ ሳያግድህ
ደርሰህ ፡ በኔ ፡ ቅጥር ፡ በራፌን ፡ ከመታህ
እከፍታለው ፡ ጌታ

ከፍቻለው ፡ በራፌን
ላስገባው ፡ ንጉሴን
አትቁም ፡ ከደጄ
እባክህ ፡ ግባ ፡ ወዳጄ

ጥያቄ ፡ የለኝም ፡ ቀረብኝ ፡ የምለው
ቤቴ ፡ የገባህ ፡ ቀን ፡ መልሴን ፡ አጊንቻለው
ምን ፡ ባደርግ ፡ ብቻ ፡ ትደሰታለህ
ፍቅሬን ፡ በመታዘዝ ፡ አሃ ፡ ገልጬ ፡ ላሳይህ

ምን ፡ ትወዳለህ ፡ አሃ ፡ ከገባህ ፡ ከቤቴ
ምን ፡ ትወዳለህ ፡ እህ ፡ ከፈለከው ፡ ሂወቴ
ማይመችህ ፡ አይሁር ፡ ሁሉም ፡ ይደልደል
ሰነባበት ፡ ኑርበት ፡ ክተም ፡ እኔ ፡ መንደር

ክብሬ ፡ ሆይ ፡ ከእግርህ ፡ ስር ፡ እሆናለው
በልቤ ፡ ላይ ፡ በቤቴም ፡ ሾሜሀለው
የማይነጥፍ ፡ የሂወት ፡ ውሀ ፡ ምንጭ
ጌታ ፡ እየሱስ ፡ አንተ ፡ የእግዚአብሄር ፡ ልጅ
ክብሬ ፡ ሆይ ፡ ከእግርህ ፡ ስር ፡ እሆናለው
ካንተ ፡ ወዴት ፡ ወደማን ፡ እንሄዳለው
የማይነጥፍ ፡ የሂወት ፡ ውሀ ፡ ምንጭ
ጌታ ፡ እየሱስ ፡ የለም ፡ ከአንተ ፡ ውጪ