ርህራሄህ (Rihraheh) - ሐምሌት ፡ በልጁን

ሐምሌት ፡ በልጁን
(Hamlet Beljun)

፪
(2)

የለሁበትም
(Yelehubetm)

ዓ.ም. (Year): 2025
ቁጥር (Track):

፲ (10)

ርዝመት (Len.): 5:00
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሐምሌት ፡ በልጁን ፡ አልበሞች
(Albums by Hamlet Beljun)

ሙግቴን ፡ የረታህ ፡ ያሸነፍህልኝ
በበደል ፡ መንገድ ፡ ላይ፣ በኀጢአት ፡ ሳልገኝ፣
መንገዴም ፡ የቀና፣ አረማመዴም ፡ ልክ፣
ሆኖ ፡ አይደል ፡ በፊት ፡ እህ ፣ በፍርድ ፡ ወንበሬ ፡ የቆምህ።
ገና ፡ ሳለሁ ፡ በኀጢአት ፡ በጨለማ ፡ መዳፍ፣
ሕይወት ፡ ሰጥተህ ፡ ፍርዴን ፡ ረታህ፤ ገልጠህ ፡ አዲስ
ምዕራፍ።

ርኅራኄህ ፡ ወደኔ ፡ አመጣህ (*2)
ይህ ፡ ቅን ፡ ልብህ ፡ እኔን ፡ ማለፍ ፡ ቢያቅተው፣
ያለምክንያት ፡ ምሕረትን ፡ አገኘሁ፤
ይህ ፡ ቅን ፡ ልብህ ፡ እኔን ፡ ማለፍ ፡ ቢያቅተው፣
ኀጢአተኛዋ ፡ ምሕረትን ፡ አገኘሁ።

በኀይል ፡ ቢሆን ፡ ከደካሞች ፡ ተራ፣
በጻድቃን ፡ ማኅበር ፡ በኀጢአተኞች ፡ ጎራ፣
የምሰለፍ ፡ እኔን ፡ ለሕይወት ፡ ልታስብ፣
ከርኅራኄህ ፡ ውጪ ፡ እህ ፡ ምንስ ፡ ሊገኝ ፡ ሰበብ?

ርኅራኄህ ፡ ወደኔ ፡ አመጣህ (*2)
ይህ ፡ ቅን ፡ ልብህ ፡ እኔን ፡ ማለፍ ፡ ቢያቅተው፣
ያለምክንያት ፡ ምሕረትን ፡ አገኘሁ፤
ይህ ፡ ቅን ፡ ልብህ ፡ እኔን ፡ ማለፍ ፡ ቢያቅተው፣
ኀጢአተኛዋ ፡ ምሕረትን ፡ አገኘሁ።

ዕድፋሙን ፡ ታሪክ ፡ ሻርክልኝ ፡ እንዳልነበር፣
ምሕረትህ ፡ አወጣ ፡ ለሕይወቴ ፡ አዲስ ፡ ጀምበር
ታምር ፡ ነው፤ ተባልሁኝ ፡ እኔም ፡ የእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ በደሌ ፡ ተሽሮ ፡ ተወግዶልኝ ፡ ፍርድ።
በኢየሱስ ፡ ቤዛነት ፡ እኔም ፡ ገባሁ ፡ ከደጅ፤
በደሌ ፡ ተሽሮ ፡ ተወግዶልኝ ፡ ፍርድ።

ምላሽ ‘ሚሆን ፡ አጣሁ ፡ ለውለታህ
ምን ፡ ደርሶ ፡ ጥግህ ፡ ላይ ፡ ምን ፡ ሊመጥንህ?
ደስ ፡ ካሰኘህ ፡ ሞልቶ ፡ በዐይንህ፣
ራሴን ፡ በመሠዊያው ፡ ላኑርልህ፤
ደስ ፡ ካሰኘህ ፡ ሞልቶ ፡ ባይንህ፣
በገዛ ፡ ዘመኔ ፡ ላገልግል ፡ ፈቃድህን።