ጠንነት ፡ ነው ፡ ወይ (Teninet New Wey) - ሐምሌት ፡ በልጁን

ሐምሌት ፡ በልጁን
(Hamlet Beljun)

፪
(2)

የለሁበትም
(Yelehubetm)

ዓ.ም. (Year): 2025
ቁጥር (Track):

፲ ፬ (14)

ርዝመት (Len.): 6:43
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሐምሌት ፡ በልጁን ፡ አልበሞች
(Albums by Hamlet Beljun)

ብዙ ፡ ብወድህ፣ ብዙ ፡ ምረኸኝ፣
አብዝቼ ፡ ብጠጋህ፣ ብዙ ፡ ትተህልኝ፣
የኔማ ፡ ፍቅር ፡ ሁሉ ፡ በምክንያት፣
ያንተ ፡ መውደድ ፡ ግን ፡ ያለ ፡ ስሌት።

ፍቅርህ ፡ ሲለካ ፡ ሲመዘን፣
ነፍስ ፡ እስከ ፡ መስጠት ፡ ሚመዝን፥
ፍቅርህ ፡ ሲመዘን ፡ ሲለካ፣
እስከ ፡ መስቀል ፡ ሞት ፡ ነው ፡ ለካ

እወድሃለሁ ፡ አምላኬ
እወድሃለሁ ፡ የኔ ፡ ሕይወት
 አንተን ፡ መውደድ ፡ ልቤ ፡ ውስጥ ፡ ያለው
የአክብሮት ፡ ፍርሀት ፡ የሞላው።
የፍቅርህን ፡ ጥልቀቱን ፡ እያሰብኩኝ
አንተን ፡ መውደድ ፡ አክብሮት ፡ ተሞላሁኝ።

ወደር ፡ የሌለው ፡ መልካምነትን፣
‘ማይመረመር ፡ ጠሊቅ ፡ ፍቅርህን፣
ይህሁሉ ፡ አይቼ ፡ ባልወድህ ፡ አይገርምም ፡ ወይ?
የማይለወጥ ፡ የማይናወጥ፣
‘ማይንሸራተት ‘ማያውቀውን ፡ ወረት
ፍቅርህን ፡ አይቼ ፡ ባልወድህ ፡ አይገርምም ፡ ወይ?
አይገርምም ፡ ወይ ፡ ባልወድህ? (*2)
ጤንነት ፡ ነው ፡ ወይ ፡ ባላመልክህ? (*2)

አንድ ፡ ቀን ፡ ቢያበቃስ ፡ ብዬ ‘ማልሠጋበት፣
ግለቱ ፡ የማይበርድ ፡ ዘመናት ፡ ቢያልፉበት፣
ከምረግጣት ፡ ምድር ፡ በላይ ‘ምታመነው፣
ጌታ ፡ ባንተ ፡ ፍቅር ፡ በማይለወጠው።

በኔ ፡ ሁኔታ ፡ ያልተጀመረ፣
በኔ ፡ አመል ፡ ጠባይ ፡ ያልተቀመረ፣
መነሻው ፡ ራስህ ፡ ከማንነትህ፣
ከፍቅር ፡ ልብህ ፡ ከመልካም ፡ ባሕርይህ።

ስበረታ ፡ አይጨምርም፤
ስደክም ፡ አይቀንስም፤
ፍቅርህ ፡ ያው ፡ ነው ፡ ዘላለም። (*2)

እወድሃለሁ ፡ አምላኬ
እወድሃለሁ ፡ የኔ ፡ ሕይወት
 አንተን ፡ መውደድ ፡ ልቤ ፡ ውስጥ ፡ ያለው
የአክብሮት ፡ ፍርሀት ፡ የሞላው።
የፍቅርህን ፡ ጥልቀቱን ፡ እያሰብኩኝ
አንተን ፡ መውደድ ፡ አክብሮት ፡ ተሞላሁኝ።

ወደር ፡ የሌለው ፡ መልካምነትን፣
‘ማይመረመር ፡ ጠሊቅ ፡ ፍቅርህን፣
ይህሁሉ ፡ አይቼ ፡ ባልወድህ ፡ አይገርምም ፡ ወይ?
የማይለወጥ ፡ የማይናወጥ፣
‘ማይንሸራተት ‘ማያውቀውን ፡ ወረት
ፍቅርህን ፡ አይቼ ፡ ባልወድህ ፡ አይገርምም ፡ ወይ?
አይገርምም ፡ ወይ ፡ ባልወድህ? (*2)
ጤንነት ፡ ነው ፡ ወይ ፡ ባላመልክህ? (*2)