ፊትህ (Fitih) - ሐምሌት ፡ በልጁን

ሐምሌት ፡ በልጁን
(Hamlet Beljun)

፪
(2)

የለሁበትም
(Yelehubetm)

ዓ.ም. (Year): 2025
ቁጥር (Track):

፮ (6)

ርዝመት (Len.): 6:06
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሐምሌት ፡ በልጁን ፡ አልበሞች
(Albums by Hamlet Beljun)

ፊት 'ማይነሳኝ ፡ ፊትህ ፡ የሚቀበለኝ
እንደ ፡ ጠዋት ፡ ፀሀይ ፡ ዘውትር ፡ ሚያሞቀኝ
ምቾቴ ፡ ነው ፡ ፊትህ ፡ ወዳንተ ፡ እሮጣለሁ
'ምትወደኝ ፡ ጌታ ፡ ፊት ፡ ነፍሴን ፡ አፈሳለሁ

ካንተ ፡ ላትለያይ ፡ ተገምዳ ፡ ህይወቴ
በምትገኝበት ፡ መኖር ፡ ነው ፡ ምቾቴ
እጅህን ፡ እይዛለሁ ፡ ላይለቅ ፡ የያዘኝን
የትም ፡ ብትሰደኝ ፡ ከኔ ፡ ጋር ፡ እስካለህ ፡ አይገደኝ

ደጃፌን ፡ ስዘጋው ፡ በመንፈስህ ፡ ልሰወር
ለካ ፡ ከዚህ ፡ ዓለም ፡ ሀሳብ ፡ እየራቅኩኝ ፡ ነበር
ቀድሞ ፡ የሚያባብለኝ ፡ የሚያስጎመጀኝ
ተራ ፡ ሆኖ ፡ አየሁት ፡ መልክህ ፡ ሲሳልብኝ

ስፈልገው ፡ ያንተን ፡ ፊት ፡ ተራመድኩኝ ፡ በጽናት
ስፈልግህ ፡ በመልካም ፡ ቀኔ ፡ አልፎኝ ፡ ሄደ ፡ ጥፋት ፡ ከኔ
ስፈልግህ ፡ ቀርበህ ፡ ሳለህ ፡ ገኖልኛል ፡ ምህረትህ
የፈለኩህ ፡ በጉብዝናዬ ፡ ዋስትናዬ ፡ ነህ ፡ ለማምሻዬ

ያንተ ፡ ፊት ፡ የኔ ፡ ምቾት
መገኘትህ ፡ ለኔ ፡ ስኬት

ፊት 'ማይነሳኝ ፡ ፊትህ ፡ የሚቀበለኝ
እንደ ፡ ጠዋት ፡ ፀሀይ ፡ ዘውትር ፡ ሚያሞቀኝ
ምቾቴ ፡ ነው ፡ ፊትህ ፡ ወዳንተ ፡ እሮጣለሁ
'ምትወደኝ ፡ ጌታ ፡ ፊት ፡ ነፍሴን ፡ አፈሳለሁ

ካንተ ፡ ላትለያይ ፡ ተገምዳ ፡ ህይወቴ
በምትገኝበት ፡ መኖር ፡ ነው ፡ ምቾቴ
እጅህን ፡ እይዛለሁ ፡ ላይለቅ ፡ የያዘኝን
የትም ፡ ብትሰደኝ ፡ ከኔ ፡ ጋር ፡ እስካለህ ፡ አይገደኝ

አሃ! የምታስብለኝ ፡ በየማለዳው
ያልደረስኩበትን ፡ እየገለጥከው
ስንቱን ፡ ለቅቄ ፡ ጣልኩኝ ፡ ወዳንተ ፡ ስል ፡ ጠጋ
ከህይወት ፡ ሚያጎድለኝን ፡ ረብ ፡ የሌለውን ፡ ዋጋ

ስፈልገው ፡ ያንተን ፡ ፊት ፡ ተራመድኩኝ ፡ በጽናት
ስፈልግህ ፡ በመልካም ፡ ቀኔ ፡ አልፎኝ ፡ ሄደ ፡ ጥፋት ፡ ከኔ
ስፈልግህ ፡ ቀርበህ ፡ ሳለህ ፡ ገኖልኛል ፡ ምህረትህ
የፈለኩህ ፡ በጉብዝናዬ ፡ ዋስትናዬ ፡ ነህ ፡ ለማምሻዬ

ያንተ ፡ ፊት ፡ የኔ ፡ ምቾት
መገኘትህ ፡ ለኔ ፡ ስኬት