አመልከዋለሁ (Amelkewalew) - ሐምሌት ፡ በልጁን

ሐምሌት ፡ በልጁን
(Hamlet Beljun)

፪
(2)

የለሁበትም
(Yelehubetm)

ዓ.ም. (Year): 2025
ቁጥር (Track):

፲ ፪ (12)

ርዝመት (Len.): 4:31
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሐምሌት ፡ በልጁን ፡ አልበሞች
(Albums by Hamlet Beljun)

ያወቅሁት ፡ እውነት ፡ ነጻ ፡ አውጥቶኛል፤
ልቤን ፡ አስከንድቶ ፡ በእምነት ፡ ያኖረኛል፤
ገብቶኛል ፡ የዘላለም ፡ ፍቅሩ፣
ተስፋ ፡ አለኝ ፡ ልካፈል ፡ ከክብሩ።

አንዳንድ ፡ መንገዶቹ ፡ ባይገቡኝ፣
ባልገነዘበው ፡ ባይመስሉኝ፣
ለጊዜው ፡ መልስ ፡ ባጣ ፡ ባይብራራልኝ፣
ጨርሼ ፡ አላውቀው ፡ ረቂቅ ፡ እግዚአብሔር፣
ግን ፡ አያናጋውም ፡ የእምነቴን ፡ ማገር።

ቀድሞንስ ፡ የምሸመድደው፣
ምኑን ፡ አምላክ ፡ ሊሆን ፡ መግቢያ ፡ መውጫውን ‘ማውቀዉ?
ግን ፡ ሳይለዋወጥ ፡ ማልዶ ፡ አዲስ ፡ እግዚአብሔር፣
ይህ ፡ ነው ፡ በመደነቅ ‘ሚያመጣኝ ፡ ከእግሩ ፡ ሥር።

አመልከዋለሁ ፡ ተደስቼ፣
አምላክ ፡ በሆነኝ ፡ በእርሱ ፡ ረክቼ። አሃ
አመልከዋለሁ ፡ ሳላቅማማ፣
እውነት ፡ ከእርሱ ፡ ወዲያ ፡ ሌላ ፡ የለማ!

እንድረዳው ፡ እንጂ ፡ እንደኔ ፡ ያከለው፣
ልኩ ፡ ሰው ፡ አይደለም፤ አምላኬ ፡ ትልቅ ፡ ነው።
ሰማይ ፡ ዙፋኑ፣ መርገጫው ፡ ምድር፣
ሙሉ ፡ ራሱን ፡ ቢገልጥ ፡ ማን ፡ ይገባው ፡ ነበር?
 “እርሱ ፡ ይህ ፡ ነው” የሚል ፡ አጥንቶ ፡ መርምሮ፣
ማን ፡ ተገኝቶ ፡ ያውቃል ፡ ከእጁ ፡ ሥራ ፡ አእምሮ?
በስሌት ፡ በቀመር ፡ ማንም ፡ አያገኘው፣
ራሱን ፡ ባይገልጥልን ፡ ሰው ፡ አይደርስበትም

አመልከዋለሁ ፡ ተደንቄ፣
ጨርሼ ፡ ስለርሱ ፡ እንደማላውቅ ፡ አውቄ፤ አሃ
አመልከዋለሁ ፡ እጄን ፡ ባፌ ፡ ጭኜ፣
ከመታወቅ ፡ የሚያልፍ ፡ መሆኑን ፡ አምኜ።

ያሁን ፡ በድንግዝግዝ ፡ ጥቂት ፡ ዕይታዬ፣
ፍጹሙ ፡ ሲመጣ ፡ ይጠራል ፡ ብዥታዬ።
ዛሬ ፡ እንደ ፡ ብልጭታ ፡ ጥቂቱ ፡ ዕይታ፣
ፍጹሙ ፡ ሲመጣ ፡ ይሆናል ፡ ወገግታ።

አመልከዋለሁ ፡ ተደስቼ፣
አምላክ ፡ በሆነኝ ፡ በእርሱ ፡ ረክቼ። አሃ
አመልከዋለሁ ፡ ሳላቅማማ፣
እውነት ፡ ከእርሱ ፡ ወዲያ ፡ ሌላ ፡ የለማ!