ትውልድ ፡ አለ (Tewled Ale) - ሐምሌት ፡ በልጁን

ሐምሌት ፡ በልጁን
(Hamlet Beljun)

፪
(2)

የለሁበትም
(Yelehubetm)

ዓ.ም. (Year): 2025
ቁጥር (Track):

፫ (3)

ርዝመት (Len.): 4:42
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሐምሌት ፡ በልጁን ፡ አልበሞች
(Albums by Hamlet Beljun)

ዘመን ፡ ሲያስብል “ድሮ ፡ ቀረ ፡ ክርስትና”
ምስሉ ፡ ጠፍቶ ፡ ደብዝዞ ፡ ከትላንና፣
ሆኖ ፡ ድብልቅ ፡ ሕዝብ ፡ መልኩ ፡ ያልጠራ፣
ግስጋሴው ፡ የሚያስፈራ።

ግን ፡ እግዚአብሔር ፡ ስለ ፡ ስሙ ፡ ግድ ፡ ይለዋል፤
በዘመናት ፡ ያለ ፡ ምስክር ፡ ራሱን ፡ መች ፡ ይተዋል?
የቤቱ ፡ ባለቤት ፡ ርስቱን ፡ አይጥልም፤
ከተኩሎቹ ፡ መሀል ፡ በጎቹ ፡ አይጠፉትም።

“ለእግዜር ፡ ትውልድ ፡ አይቅር ፡ ብለው ፡ የማሉ
መሠዊያን ፡ አፍርሰው ፡ ኪዳንን ፡ የተዉ
ነቢያትን ፡ አጠፉ ፡ በክፋት ፡ ዘመቻ
ተስፋ ፡ ቆርጫለሁ፤ ቀርቼ ፡ እኔ ፡ ብቻ!”
ኀይሉ ፡ ሁሉ ፡ ተሟጥጦ ፡ ለፈራው ፡ ኤሊያስ
ከሰማያት ፡ መጣ ፡ አምላካዊ ፡ መልስ
 “ቅሬታ ፡ አለኝ ፡ ከትውልዱ፣
ለባዕዳን ፡ ያልሰገዱ፣
ጉልበታቸው ፡ ያልተበላ፣
 ‘ማያምራቸው ፡ ወደኋላ”
እንደ ፡ አብድዩ ፡ አሉ ፡ ወገን
‘ሚያስመልጡ ፡ ትውልድ ፡ በቁርጥ ፡ ቀን
እንደ ፡ ዮዳሄ ፡ አሉ ፡ አባቶች፣
የሚያወርሱ ፡ የአምላክ ፡ ሥርዐት።

የቤቱ ፡ ባለቤት ፡ ርስቱን ፡ አይጥልም፤
ከተኩሎቹ ፡ መሀል ፡ በጎቹ ፡ አይጠፉትም።

አለው ፡ ትውልድ ፡ ዛሬም፣
በድብልቅ ፡ ዘመን ፡ ያልተበራረዙ፣
በጠባቡ ፡ መንገድ ፡ እውነትን ፡ የያዙ፣
በሁለት ፡ ሀሳብ ‘ማያነክሱ፣
ዐመፃን ፡ እጅ ፡ ያልነሱ፣
በነፍሳቸው ፡ የቆረጡ፣
በጽድቅ ፡ ወንጌል ፡ ያልቀየጡ፣
አተኩረው ፡ ብድራትን፣
የናቁ ፡ ይህች ፡ ዓለምን፣
ተሥሎ ፡ መስቀል ፡ በልባቸው፣
የእግዜር ፡ ጠላት ፡ ጠላታቸው።

አለው ፡ ዛሬም ፡ ትውልድ፣
ልገኝ ፡ እኔም ፡ ሲባል ፡ አንድ።
አልቀር ፡ በትዝታ፣ አልኖርም ፡ በምኞት
ትናንት ፡ የነበረው ፡ እግዚአብሔር ፡ ምን ፡ ተስኖት!
ልሁን ፡ የክብር ፡ ዕቃ ፡ እንጂ ፡ ልገኝ ፡ እኔ፣
አለ ፡ ሕያው ፡ ክንዱ ፡ ዛሬም ፡ በዘመኔ።

የእምነት ፡ ጋሻን ፡ አነሣለሁ
የመንፈስ ፡ ሰይፍ ፡ እመዝዛለሁ
 እውነት ፡ ሆኖ ፡ ዝናሬ
በጽድቅ ፡ ወንጌል ፡ ጸንቶ ፡ እግሬ