ሁሌ ፡ የሚገርመኝ ፡ የሚደንቀኝ ፡ አንድ ፡ ነገር
ተጠቅልላ ፡ በምታልፍ ፡ ምድር ፡ መታሰቤ ፡ በእግዚአብሔር
እኔን ፡ የሚገርመኝ ፡ የሚደንቀኝ ፡ አንድ ፡ ነገር
ተጠቅልላ ፡ በምታልፍ ፡ ምድር ፡ መታሰቤ ፡ በእግዚአብሔር
ይህንን ፡ አይተ ፡ ይህንን ፡ ቆትረ ፡ ቢዬ ፡ ምለው ፡ ስለሌለኝ
እጄን ፡ በአፌ ፡ ጭናለሁ
ጸጋ ፡ ከመጠን ፡ አልፎ ፡ ምህረት ፡ ከሐጢያቴ ፡ ገዝፎ
በገዛ ፡ መንገዴ ፡ ስዳክር ፡ ሳብከኝ ፡ ወደ ፡ እረፍቴ ፡ በፍቅር
ዓለም ፡ ሳይፈጠር ፡ የወሰንከኝ ፡ የጸጋ ፡ ክብር ፡ እንዲመሰገን
ሁሉ ፡ ባንተ ፡ ካንተ ፡ ሆነልኝ ፡ ምን ፡ አዋጣሁኝ ፡ እንድትወደኝ
የለሁበትም ፡ ለመዳኔ
የለሁበትም ፡ ለመመረጤ
እጄ ፡ የለበትም ፡ ከሆነው ፡ ቸርነት
ስምህ ፡ ይባረክ ፡ ሁሉ ፡ ባንተ ፡ ምህረት
የለሁበትም ፡ ለመወደዴ
የለሁበትም ፡ ለመማሬ
እጄ ፡ የለበትም ፡ ከሆነው ፡ ቸርነት
ስምህ ፡ ይባረክ ፡ ሁሉ ፡ ባንተ ፡ ምህረት
አመሰግናለው ፡ አመሰግናለው
አመሰግናለው ፡ ሲገርመኝ ፡ ኖራለው
አመሰግናለው ፡ አመሰግናለው
አመሰግናለው ፡ ሲደንቀኝ ፡ ኖራለው
በመዳፍህ ፡ ሽንቁ ፡ በዛ ፡ የመስቀል ፡ ጣር
ተገኘች ፡ ሕይወቴ ፡ አምልጣ ፡ ከሞት ፡ ባህር
እኔ ፡ ተቀበልኩኝ ፡ በነጻ ፡ ድህነትህ
ዓብ ፡ ግን ፡ ከፍሎበት ፡ ነው ፡ አንዲያ ፡ ዉድ ፡ ልጁን
የለሁበትም ፡ ለመዳኔ
የለሁበትም ፡ ለመመረጤ
እጄ ፡ የለበትም ፡ ከሆነው ፡ ቸርነት
ስምህ ፡ ይባረክ ፡ ሁሉ ፡ ባንተ ፡ ምህረት
የለሁበትም ፡ ለመወደዴ
የለሁበትም ፡ ለመማሬ
እጄ ፡ የለበትም ፡ ከሆነው ፡ ቸርነት
ስምህ ፡ ይባረክ ፡ ሁሉ ፡ ባንተ ፡ ምህረት
አመሰግናለው ፡ አመሰግናለው
አመሰግናለው ፡ ስገዛ ፡ ኖራለው
አመሰግናለው ፡ አመሰግናለው
አመሰግናለው ፡ ሳመልክህ ፡ ኖራለው