ዕድልን ፡ ሰጥተኸኝ ፡ ብኖር ፡ ብዙ ፡ ዘመን፣
በዕድሜዬ ፡ ማምሻ ፡ ኑሮዬ ፡ ሲመዘን፣
አንገት ‘ምደፋበት ፡ በሐፍረት ፡ የማስበው፣
ቀናት ፡ ዓመት ፡ አይኑር ፡ ታሪኬን ‘ሚያጎድፈው፤
መሻቴ ፡ በክብር ፡ ማብቃት ፡ ሩጫዬን፣
ታማኝ ፡ ባሪያ ፡ መባል፣ ከእጅህም ፡ አክሊሌን።
የማይለወጥ ፡ ልመናዬ፣
የማልሽረው ፡ ጽኑ ፡ መሻቴ፣
ሁሌም ፡ በቤትህ ፡ እንድኖር፤
እርምጃዬ ፡ ፊትህ ፡ እንዲያምር።
ፍፃሜዬ ፡ ፊትህ ፡ እንዲያምር።
ያልተመሠረተ ፡ ጸንቶ ፡ በዐለቱ፣
ንፋስ ፡ ጎርፍ ፡ ሲመጣ ፡ አሃሃ ፡ ታላቅ ፡ ነው ፡ ውድቀቱ።
እስከ ፡ መኸር ፡ ቢዘልቅ ፡ እንክርዳድ ፡ ከስንዴው፣
አይገባ ፡ ጎተራ፣ አሃሃ ፡ በእሳት ፡ መደምደሚያው።
በፊትህ ፡ ጸሎቴ ፡ ሞገስ ፡ ያግኝ፤
በፍጻሜ ፡ ማማር ፡ እባክህ ፡ ባርከኝ። (*2)
ድንገት ፡ ሄጄ ፡ ሄጄ ፡ ልቤ ፡ እንዳይከዳኝ፣
በሰው ፡ የጠላሁት ፡ በቤቴ ፡ እንዳይገኝ፣
የፈራሁት ፡ ያንን ፡ ሆኜው ፡ እንዳልገኝ፤
ብርታቴ ፡ ሆይ፤ አንተ ፡ የማምለጫ ፡ ዐለቴ፣
ከጸጋህስ ፡ በቀር ፡ ምን ፡ ሊሆን ፡ ትምክህቴ? (*2)
ነፍሴ ፡ ስትዝል፣ ስትደክምብኝ፣
የኀጢአትን ፡ ጽዋ ፡ እንዳትጠጣብኝ፣
እስከ ፡ ሞት ፡ ታግሦ ፡ በአብ ፡ ቀኝ ፡ ያለውን፣
አስታውሳታለሁ ፡ የእምነቴን ፡ ራስ ፡ ፈጻሚው ፡ ኢየሱስን።
ባክኖ ፡ እንደማይቀር ፡ ተጋድሎዬ ፡ መና፣
የአባቶች ፡ ምስክር ፡ ሆኖ ፡ እንደ ፡ ደመና፣
ያጽናናታል ፡ ነፍሴን ፡ የድል ፡ ታሪካቸው፣
በተስፋ ፡ የታገሡ ፡ ከእጁ ፡ ነው ፡ ዋጋቸው።
እስክትመጣ ፡ እስካይህ፣
እስክሸለም ፡ ከእጆችህ፣
በተስፋ ፡ ቃል ፡ እጽናናለሁ፤
በጸጋህም ፡ እመካለሁ።