አደራ ፡ ነው (Adera New) - ሐምሌት ፡ በልጁን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search
ሐምሌት ፡ በልጁን
(Hamlet Beljun)

፩
(1)

እለምንሃለሁ
(Eleminihalew)

ዓ.ም. (Year): 2019
ቁጥር (Track):

፲ (10)

ርዝመት (Len.): 4:44
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሐምሌት ፡ በልጁን ፡ አልበሞች
(Albums by Hamlet Beljun)

በስልጣንህ ፡ ቃል ፡ ዓለምን ፡ በያዝከው
የህይወቴን ዳርቻ ፡ ዘመን ፡ በወሰንከው
ባንተ ፡ ህያው ፡ ሆኜ ፡ ወጣለው ፡ ገባለው
እንኳን ፡ በእጄ ፡ የያዝኩት ፡ እስትንፋሴም ፡ ያንተው ፡ ነው

ማስተዋልን ፡ ስጠኝ
ኢየሱስ ፡ ሆይ ፡ አስበኝ
ማስተዋልን ፡ ስጠኝ
ጌታዬ ፡ አስበኝ

ያለው ፡ ተከማችቶ ፡ ሲሞላ ፡ ጎተራው
መሰለው ፡ ዘመኑን ፡ መንዝሮ ፡ ሚበላው
ተላላ ፡ አላዋቂ ፡ ሆኖ ፡ አለፈች ፡ ነፍሱ
ሲሻ ፡ ዘላለሙን ፡ ታምኖ ፡ ሊኖር ፡ ራሱን
ታምኖ ፡ ሊኖር ፡ ኪሱን
ጉልበቱን ፡ ባልሳመ ፡ ክንዱን ፡ ባልተመካ
ብርታት ፡ የሰጠውን ፡ አምላኩን ፡ ቢረዳ
እድሜው ፡ እንደ ፡ እንፋሎት ፡ ነው ፡ ለካ

እርዳኝ ፡ እኔን ፡ አዎ
አግዘኝ ፡ እኔን ፡ አዎ
እንድታመንልህ ፡ አዎ
ደስ ፡ እንዳሰኝህአዎ

የላቡን ፡ ዋጋ ፡ ፍሬ ፡ ሚጠብቅ
የለፋ ፡ ሰው ፡ ነው ፡ ደሞዝ ፡ የሚጠይቅ
እንዲሁ ፡ በነፃ ፡ ፀጋን ፡ ስትሰጠኝ
ባልደከምኩበት ፡ ተመን ፡ ካወጣሁኝ
ያን ፡ ጊዜ ፡ ውድቀት ፡ ከጀለኝ
አደራህን ፡ ከእጄ ፡ ምትቀበልበት
ቀን ፡ አለ ፡ በፊትህ ፡ የምጠየቅበት
ነህና ፡ የሁሉ ፡ ባለቤት

እርዳኝ ፡ እኔን ፡ አዎ
አግዘኝ ፡ እኔን ፡ አዎ
እንድታመንልህ ፡ አዎ
ደስ ፡ እንዳሰኝህአዎ

እንዲሁ ፡ መጣሁ ፡ እንዲሁ ፡ ሄዳለው
ሁሉን ፡ የሰጠኝ ፡ በአደራ ፡ ነው
ትምክህቴ ፡ ታዲያ ፡ በምን ፡ ነው
ሁሉ ፡ እኮ ፡ የእግዚአብሄር ፡ ነው
አክብሬ ፡ ስኖር ፡ አደራዬን
እቀበላለው ፡ ሽልማቴን
ናፍቆት ፡ የልቤ ፡ ጥማት
ታማኝ ፡ ባሪያ ፡ ሲለኝ ፡ መስማት

የሁሉ ፡ አደራ ፡ ነዉ ፡ አዎ
የተቀበልኩት ፡ አዎ
አንድ ፡ ቀን ፡ ፊቱ ፡ አዎ
ምጠየቅበት ፡ አዎ
(ማስተዋልን ፡ ስጠኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ሆይ ፡ አስበኝ
ማስተዋልን ፡ ስጠኝ ፡ ጌታዬ ፡ አስበኝ)