እወድሃለሁ (Ewedihalew) - ሐምሌት ፡ በልጁን

ሐምሌት ፡ በልጁን
(Hamlet Beljun)

፩
(1)

እለምንሃለሁ
(Eleminihalew)

ዓ.ም. (Year): 2019
ቁጥር (Track):

፯ (7)

ርዝመት (Len.): 5:28
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሐምሌት ፡ በልጁን ፡ አልበሞች
(Albums by Hamlet Beljun)

ካወኩህ ፡ ጀምሮ ፡ ከተጠጋሁህ
በጥላህ ፡ ስር ፡ ሳድር ፡ አንተን ፡ ካመንኩህ
የማውቀው ፡ ይኼን ፡ ነው ፡ ስላንተማንነት
ተረትም ፡ አይደለም ፡ በአይኔ ፡ ያየሁት ፡ እውነት

አይሰለችህም ፡ ስትወደኝ
አይሰለችህም ፡ ስትምረኝ
አይሰለችህም ፡ ለኔ ፡ መራራት
አልታከተህም ፡ እኔን ፡ ለመርዳት
አይሰለችህም ፡ ከኔ ፡ ጋር ፡ መሆን
አይሰለችህም ፡ ማድመጥ ፡ ውስጠቴን
አይሰለችህም ፡ ስትመራኝ
አልታከተህም ፡ ስትሸከመኝ


ምን ፡ እልሃለሁ ፡ ቃሌ ፡ ደካማ ፡ ነው
አዉጥቼ ፡ አውርጄ ፡ ምለው ፡ አጣው
ብቻ ፡ እወድሃለሁ

እውነትህ ፡ ሲፈርድ ፡ ሐጢያት ፡ በደሌን ፡ ገልጦ
ምህረትህ ፡ ከደነው ፡ እኔን ፡ መውደድህ ፡ በልጦ
ፍቅር ፡ ምክኒያት ፡ ሆኖ ፡ ፊትህ ፡ አቀረበኝ
አንተ ፡ ጋር ፡ የሚያስጠጋኝ ፡ ሌላማ ፡ ምን ፡ ብቃት ፡ ነበረኝ
የፀጋህ ፡ ጉልበት ፡ ወዳንተ ፡ አቀረበኝ
አንተ ፡ ጋር ፡ ሚያስጠጋኝ ፡ ሌላማ ፡ ምን ፡ ድፍረት ፡ ነበረኝ

ምን ፡ እልሃለሁ ፡ ቃሌ ፡ ደካማ ፡ ነው
አዉጥቼ ፡ አውርጄ ፡ ምለው ፡ አጣው
ብቻ ፡ እወድሃለሁ
እኔ ፡ እወድሃለሁ ፡ እኔ ፡ እወድሃለሁ
ውስጤ ፡ ያለው ፡ ብዙ ፡ ነዉ
ቃሌ ፡ ግን ፡ ትንሽ ፡ ነዉ

እራርተህልኝ ፡ እየታገስከኝ
ይቅር ፡ እያልከኝ ፡ ብዙ ፡ ምረኸኝ
ዛሬ ፡ አደረስከኝ
እየመከርከኝ ፡ እየገሰፅከኝ
በክንፍህ ፡ ሸፍነህ ፡ እጄን ፡ ይዘኸኝ
ዛሬ ፡ አደረስከኝ

ምን ፡ እልሃለሁ ፡ ቃሌ ፡ ደካማ ፡ ነው
አዉጥቼ ፡ አውርጄ ፡ ምለው ፡ አጣው
ብቻ ፡ እወድሃለሁ
እኔ ፡ እወድሃለሁ ፡ እኔ ፡ እወድሃለሁ
ውስጤ ፡ ያለው ፡ ብዙ ፡ ነዉ
ቃሌ ፡ ግን ፡ ዉስን ፡ ነዉ

 ትላንቴ ፡ ያለፈው ፡ በበጎነትህ
 አምና ፡ ካቻምናዬም ፡ ቢያወሩ ፡ ምህረት ፡ ቸርነትን
 አሁንም ፡ ምኖረው ፡ አንተን ፡ ተማምኜ
ማይንሸራተተው ፡ ፍቅርህነው ፡ ዋስትና ፡ ማህተሜ

አትለወጥም ፡ ለዘለዓለም
አትቀየርም ፡ ስለዚህ ፡ ነገን ፡ አልፈራም
አንተ ፡ እኮ ፡ አትለዋወጥም
ነገን ፡ አልፈራ ፡ እኔም
አንተ ፡ እንደው ፡ አትቀያየርም
ነገን ፡ አልፈራ ፡ እኔም