አትለፈኝ (Atilefegn) - ሐምሌት ፡ በልጁን

ሐምሌት ፡ በልጁን
(Hamlet Beljun)

፩
(1)

አልበም
(Eleminihalew)

ዓ.ም. (Year): 2019
ቁጥር (Track):

፪ (2)

ርዝመት (Len.): 4:47
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሐምሌት ፡ በልጁን ፡ አልበሞች
(Albums by Hamlet Beljun)

ክብር ፡ ሞገሴ ፡ ግርማ ፡ ድምቀቴ ፡ ውበቴ
አለኝታዬ ፡ ጋሻ ፡ መከታ ፡ ዋስትናዬ
የሆነው ፡ ፊትህ ፡ የምናፈቀው ፡ ምወደው
ከሁሉ ፡ በላይ ፡ ህልውናህን ፡ ነው ፡ ምፈልገው

       በፊትህ ፡ ስሆን ፡ ነዉ ፡ ደስታዬ
       በፊትህ ፡ መዋረድ ፡ ነው ፡ ክብር ፡ እርካታዬ
       በፊትህ ፡ ስሆን ፡ ነው ፡ አቅሜ
       ነፍሴን ፡ ሳፈስ ፡ ነው ፡ ሚበዛው ፡ ሰላሜ

ዛሬም ፡ በፊትህ ፡ ደስ ፡ ብሎኝ ፡ እመጣለሁ
አባቴ ፡ ልልህ ፡ ጓጉቼ ፡ እመጣለሁ
ከእጅህ ፡ ሳይሆን ፡ አንተን ፡ ፈልጌ ፡ እመጣለሁ
የማለምደውን ፡ ክብር ፡ ናፍቄ ፡ መጣለሁ
ዛሬም ፡ በፊትህ ፡ ደስብሎኝ ፡ እመጣለሁ
አዲስነትህ ፡ አጓጉቶኝ ፡ እመጣለሁ
ከእጅህ ፡ ሳይሆን ፡ አንተን ፡ ፈልጌ ፡ እመጣለሁ
የማለምደውን ፡ ክብር ፡ ናፍቄ መጣለሁ

 አተለፈኝ ፡ ሳትነካኝ
በመገኘትህ ፡ ሳትባርከኝ
ህልውናህን ፡ አትንፈገኝ
ጩኸቴ ፡ ፊትህ ፡ ሞገስካገኘ ፡ እባክህ ፡ ዳሰኝ
አተለፈኝ ፡ ሳትነካኝ
በመገኘትህ ፡ ሳትባርከኝ
ህልውናህን ፡ አትንፈገኝ
ጨለማው ፡ ብርሀን
በረሀው ፡ ለምለም ፡ እንዲሆንልኝ

አንዴ ፡ ከሰጠኸኝ ፡ ድፍረት
ለመቅረብ ፡ ወዳለህበት
ህልውናህን ፡ እሻዋለው
ክብርህን ፡ ስተገልጥ ፡ ላይ ፡ እወዳለው

ባለህበት
ፍፁም ፡ ህይወት
ፍፁም ፡ እርካታ ፡ ፍፁም ፡ ሙላት
 ባለህበተ ፡ ፍፁም ፡ ደስታ
ይሞላኛል ፡ ሰላም ፡ እረፍት