ጉልበቴ ፡ ሆይ (Gulbete Hoy) - ሐምሌት ፡ በልጁን

ሐምሌት ፡ በልጁን
(Hamlet Beljun)

፩
(1)

እለምንሃለሁ
(Eleminihalew)

ዓ.ም. (Year): 2019
ቁጥር (Track):

፲ ፬ (14)

ርዝመት (Len.): 5:29
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሐምሌት ፡ በልጁን ፡ አልበሞች
(Albums by Hamlet Beljun)

የወደቀ ፡ ዳግም ፡ አይነሳም ፡ ወይ
የሳተስ ፡ ከፊቱ ፡ ደግሞ ፡ አይቆምም ፡ ወይ
አይኑ ፡ እንዳየ ፡ አይበይን ፡ ጆሮው ፡ እንደ ፡ ሰማ
የምስኪኑን ፡ ጩኸት ፡ አይቶ ፡ አያልፍ ፡ እሱማ

መስቀል ፡ ተሸክሞ ፡ መከተል ፡ ሲያቅተኝ
በጠባቡ ፡ መንገድ ፡ መጓዝ ፡ ሲሳነኝ
ነፍሴ ፡ እጅጉን ፡ ዝላ ፡ ተስፋዬ ፡ ተሟጦ
በትዕዛዛትህ ፡ ለመሄድ ፡ ውስጤ ፡ አቅም ፡ አጥቶ
የላሉ ፡ እግሮቼን ፡ ጉልበቴን ፡ አፀናህ
ዳግም ፡ እንደንስር ፡ ሃይሌን ፡ አደስክና

ጉልበቴ ፡ ሆይ ፡ ክበር ፡ ክበር
አቅሜ ፡ ሆይ ፡ ክበር ፡ ክበር
ዛሬም ፡ ረድተኸኛል ፡ እግዚአብሔር
ዛሬም ፡ አግዘኸኛል ፡ እግዚአብሔር
አቅሜ ፡ ሆንክልኝ እግዚአብሔር
ጉልበቴን ፡ አፀናህ ፡ እግዚአብሔር

ከበአል ፡ ነቢያት ፡ እንዳልተወራረደ
በኤልዛቤል ፡ ዛቻ ፡ ልቡ ፡ ወዲያው ፡ ራደ
ጥለኸው ፡ አላለፍክ ፡ ብርቱ ፡ ሰው ፡ ፍለጋ
የቀደመው ፡ ስራው ፡ ቅናቱ ፡ እንደሌለው ፡ ዋጋ
የፍቅር ፡ እንጎቻህን ፡ ዳግም ፡ ብላ ፡ አልከው
እረጅሙን ፡ ጉዞ ፡ በድል ፡ ወደህ ፡ ልታስጨርሰው

ለደካማው ፡ ሃይልን ፡ ይሰጣልና
ለወደቀ ፡ እጁን ፡ ዘርግቷልና
ዘወትር ፡ ሊረዳን ፡ እርሱ ፡ ታምኗልና
ይክበር ፡ ዘላለም ፡ ይብዛለት ፡ ምስጋና

ዛሬም ፡ ይረዳናል እግዚአብሔር
ዛሬም ፡ ያግዘናል እግዚአብሔር
አቅማችን ፡ ሆኗል እግዚአብሔር
ጉልበታችን ፡ ፀንቷል በእግዚአብሔር