መዳኛ (Medagna) - ሐምሌት ፡ በልጁን

ሐምሌት ፡ በልጁን
(Hamlet Beljun)

፩
(1)

እለምንሃለሁ
(Eleminihalew)

ዓ.ም. (Year): 2019
ቁጥር (Track):

፲ ፩ (11)

ርዝመት (Len.): 3:15
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሐምሌት ፡ በልጁን ፡ አልበሞች
(Albums by Hamlet Beljun)

የቅዱሳን ፡ ልብ ፡ ይታመንብሃል
በጎነቱ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ይጠባበቅሃል
ጌታዬ ፡ ባንተ ፡ የተያዘ
አይጠፋም ፡ ባንተ ፡ ታገዘ

ይምጣ ፡ ይወራረድ ፡ አህዛብ ፡ አምላካቹ
የኔም ፡ ጌታ ፡ ይኸው ፡ ግርማው ፡ ይታያቹ
ልቆ ፡ ከፍ ፡ የሚለው ፡ ይውሰድ ፡ መስዋቱን
ይቀበል ፡ ምስጋና ፡ የአምላክነት ፡ ክብሩን

ሲል ፡ ለተወራረደ ፡ በስምህ ፡ ጀግኖ
ሃይልህ ፡ በዕርሱ ፡ ታየ ፡ ክብርህ ፡ በላዩ ፡ ዳምኖ
ባንተ ፡ የታመነውን ፡ በድል ፡ አሸለልከው
ክብርህን ፡ ስትገልጠው ፡ ስጋ ፡ ለባሸ ፡ አየው

አምላክነትህ ፡ ይታይ ፡ በእኛም
ስለሆንከን ፡ ፅኑ ፡ መዳኛ
መዳኛ ፡ መዳኛ ነህ
ማምለጫ ማምለጫ ፡ ነህ

የአብርሃም ፡ የይስሀቅ ፡ የያዕቆብ ፡ አምላክ
ዛሬም ፡ በክርስቶስ ፡ የቅዱሳን ፡ አባት
ስምህ ፡ እቃ ፡ ጦራችን ፡ ይዘን ፡ እንወጣለን
ሞገስ ፡ ክብራችን ፡ ነህ ፡ እንታመንሃለን

አባትነትህ ታየ ፡ በኛ
ስለሆንከን ፅኑ ፡ መዳኛ
መዳኛ ፡ መዳኛ ነህ
ማለፊያ ፡ ማረፊያ