ከእልፍኟ ፡ ማልዳ ፡ ፀሀይ ፡ ስትወጣ
ታበስር የለ ፡ ወይ ፡ ሌላ ፡ ቀን ፡ እንደመጣ
የእግዚያብሔር ፡ ምህረት ፡ የተገለጠባት
ለሀጥዕ ፡ ለፃድቁ ፡ አድሎ ፡ በሌለበት
ትእግስቱን ፡ ትሰብካለች ፡ የርህራሄውን ፡ ስፋት
ትላለች ፡ ይኼው ፡ ሌላ ፡ ቀን ፡ እግዚአብሔር ፡ ያወጣት
በቅድስናህ ፡ ፊት ፡ ማን ፡ መቆም ፡ ይችላል
እንኳን ፡ ስጋ ፡ ለባሽ ፡ ተራራውም ፡ ጤሷል
ነውር ፡ በሌለበት ፡ በአዲስ ፡ ኪዳኑ ፡ በግ
ወደ ፡ ፀጋው ፡ ዙፋን ፡ ተቻለ ፡ በእምነት ፡ መቅረብ
ኦሆ ፡ እንዳንተ ፡ መሀሪ ፡ የለም*2
ኦሆ ፡ እንዳንተ ፡ ይቅር ፡ ባይ ፡ የለም*2
የሀጥያታችን ፡ ብዛት ፡ ቁጣህን ፡ ቢያነደው
ምትክ ፡ ሆኖ ፡ እየሱስ ፡ በላዩ ፡ አበረደው
ፃድቅ ፡ ሆኖ ፡ ሳለ ፡ ሃጥያት ፡ የማያውቀው
የሁላችንን ፡ በደል ፡ በሱላይ ፡ አኖርከው
እዳችንን ፡ ሊከፍል ፡ ደቀቀ ፡ ቆሰለ
መድሀኒአለም ፡ በመስቀል ፡ ላይ ፡ ዋለ
ምህረቱ ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ ለዘላለም ፡ ነው
ይቅርታው ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ ለዘላለም ፡ ነው
ርህራሄው ፡ አያልቅም ፡ ለዘላለም ፡ ነው
ማለዳ ፡ አዲስ ፡ ነው ፡ ለዘላለም ፡ ነው