እናመልክሀለን (Enamelkihalen) - ሐምሌት ፡ በልጁን

ሐምሌት ፡ በልጁን
(Hamlet Beljun)

፩
(1)

እለምንሃለሁ
(Eleminihalew)

ዓ.ም. (Year): 2019
ቁጥር (Track):

፭ (5)

ርዝመት (Len.): 5:06
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሐምሌት ፡ በልጁን ፡ አልበሞች
(Albums by Hamlet Beljun)

እንዴት ፡ ሰው ፡ አንተን ፡ ከማምለክ ፡ ኃላ ፡ ይቀራል
ምክኒያት ፡ የለኝም ፡ ቢል ፡ እንኳን ፡ ፍጥረት ፡ ይበቃል
የእጅህን ፡ ስራ ፡ እያየን ፡ እናደንቅሀለን
እኔና ፡ ቤቴ ፡ ግን ፡ እግዚያብሄር ፡ ሆይ ፡ እናመልክሀለን

በዝማሬ ፡ እናመልክሀለን
በእልልታ ፡ እናመልክሀለን
ዝቅ ፡ እያልን ፡ እናመልክሀለን
በደስታ ፡ እናመልክሀለን

ሁሉን ፡ ስትሰራ ፡ አጋዥ ፡ አላሻህም ፡ ረዳት ፡ አልጠራህም
ብቻህን ፡ ፈጠርክ ፡ በሀይል ፡ በችሎትህ
ለቃልህ ፡ ታዞልህ
ቀላያት ፡ ፈጠርክ ፡ በአፍህ ፡ ቃል
ምድርን ፡ አፀናህ  በአፍህ ፡ ቃል
ጨረቃን ፡ ለሊት ፡ ሾመሀታል
ቀኑን ፡ ስትጠራ ፡ ፀሀይ ፡ ወጥቷል

ኦ ፡ ጥበብህ ፡ ኦ ፡ ስራህ
ኦ ፡ ችሮታህ ፡ ኦ ፡ እውቀትህ
ባለጠግነትህ ፡ ጥልቅ ፡ ነው
ጥበብ ፡ እውቀትህ ፡ ጥልቅ ፡ ነው
ሰማይ ፡ ምድሩ ፡ ያንተ ፡ ነው
ሀይልም ፡ ስልጣንም ፡ በእጅህ ፡ ነው

እንዳንተ ፡ ያለ ፡ ማንም ፡ እንደሌለ ፡ ሰምቼ ፡ ነበረ
አየችህ ፡ አይኔ ፡ ልዑል ፡ ካንተ ፡ ሌላ ፡ እንደሌለ ፡ የከበረ
ገናናነትህን ፡ አወራለሁ
አምላክነትህን ፡ አወራለሁ
ሀይልህን ፡ ብርታትህን ፡ አወራለሁ
ኤልሻዳይ ፡ መሆንህን ፡ አይቻለዉ

ኦ ፡ ጥበብህ ፡ ኦ ፡ ስራህ
ኦ ፡ ችሮታህ ፡ ኦ ፡ እውቀትህ
ባለጠግነትህ ፡ ጥልቅ ፡ ነው
ጥበብ ፡ እውቀትህ ፡ ጥልቅ ፡ ነው
ሰማይ ፡ ምድሩ ፡ ያንተ ፡ ነው
ሀይልም ፡ ስልጣንም ፡ በእጅህ ፡ ነው