ነነዌ ፡ በሀጥያት ፡ ተዉጣ ፡ ተከባ
ሊያጠፋት ፡ ሲነሳ ፡ ህዝቡ ፡ ቢመለስ ፡ በብዙ ፡ ንስሀ
ቁጣውን ፡ አርቆ ፡ ምህረቱን ፡ አብዝቶ ፡ ህዝቡን ፡ ቢያስበው
ባርያው ፡ ማዘኑ ፡ ጌታን ፡ መሞገቱ ፡ እኮ ፡ ለምንነው
እግዚአብሄር ፡ ምህረቱ ፡ ሰፊ ፡ ነዉ
እግዚአብሄር ፡ ምህረቱ ፡ ጥልቅ ፡ ነዉ
ቅሉ ፡ ድንገት ፡ በቅሎ ፡ ከስሞ ፡ እጄ ፡ ቢያደርቀው
ክንድህ ፡ ላለፋበት ፡ ልብህ ፡ ከጨነቀው
እንዴትስ ፡ አይራራም ፡ አያዝነለት ፡ ልቤ
ግራና ፡ ቀኙን ፡ ለማያውቀው ፡ ህዝቤ
አለው ፡ እግዚአብሄር ፡ መሀሪ ፡ ነው
ይምራል ፡ ይታደጋል ፡ ይቅር ፡ ይላል
በእውነት ፡ ለሚመለስ ፡ ጌታ ፡ እኮ ፡ ይራራል
ያዝንለታል
ይምራል ፡ ይታደጋል ፡ ይቅር ፡ ይላል
በህዝቡ ፡ ድካም ፡ እሱ ፡ መች ፡ ይስቃል ፡ ይሳለቃል
አምላኩ ፡ ቢቀባው ፡ ጠላት ፡ ፊት ፡ አክብዶ
ህዝቡን ፡ የሚታደግ ፡ መስፍን ፡ ሊያደርገው ፡ ወዶ
ተጠልፎ ፡ ቢወድቅ ፡ በደሊላ ፡ ውጥን
አልነፈገው ፡ ሰጠው ፡ ዳግም ፡ ምህረቱን
በሞቱ ፡ እልፍ ፡ አስጣለው ፡ አስቦት ፡ ባሪያውን
በእውነት ፡ ለሚመለስ ፡ መሀሪ ፡ ነው
መንፈሱን ፡ ለሰበረ ፡ አዛኝ ፡ ነው
በቃሉ ፡ ለሚርድ ፡ ለትሁት ፡ ሰው
እጅግ ፡ ያበዛታል ፡ ምህረቱን
ይምራል ፡ ይታደጋል ፡ ይቅር ፡ ይላል
የእንደገና ፡ አምላክ ፡ እግዚአብሔር ፡ ይራራል ፡ ይቅር ፡ ይላል
ይምራል ፡ ይታደጋል ፡ ይቅር ፡ ይላል
በህዝቡ ፡ ድካም ፡ እሱ ፡ መች ፡ ይስቃል ፡ ይሳለቃል