ዛሬም ፡ እግሮችህ ፡ ስር ፡ ቁጭ ፡ እላለሁ
የነፍሴ ፡ ርሃቧም ፡ ይሄው ፡ ነው
ቃል ፡ ይውጣ ፡ ተናገር ፡ ካፍህ
እኔም ፡ እሰማለው ፡ ድምፅህን
በቃልህ ፡ ተናገረኛ
እኔም ሰማሀለው ፡ ዝም ፡ አትበለኛ
በለኛ ፡ ተናገረኛ
እኔም ፡ ሰማሀለው ፡ ዝም ፡ አትበለኛ
ሰው ፡ ከእግዚያብሔር ፡ አፍ ፡ በሚወጣ ፡ ቃል
እንጂ ፡ በእህል ፡ ውሃ ፡ ብቻ ፡ መች ፡ ይኖራል
ተስፋ ፡ አተው ፡ የደረቁ ፡ አጥንቶች ፡ ቆመዋል
ካፉ ፡ ቃል ፡ ሲወጣ ፡ ለምልመው ፡ ታይተዋል
የህይወት ፡ ምንጭ ፡ ነው ፡ ቃልህ
ልብ ፡ ያቀናል ፡ ደግሞም ፡ ምክርህ
ማይለወጥ ፡ ሚለዉጥ ፡ ቃልህ
ይምጣ ፡ ይፍሰስ ፡ በማደሪያህ
ቃልህ ፡ ፍፁም ፡ እውነት ፡ ቃልህ ፡ ፍፁም ፡ ህይወት
ወጥቷል ፡ እና ፡ ከአንተ ፡ አንደበት
ምን ፡ ስህተት ፡ ሊገኝበት
ቃልህ ፡ ፍፁም ፡ እውነት ፡ ቃልህ ፡ ፍፁም ፡ ህይወት
ወጥቷል ፡ እና ፡ ከአንተ ፡ አንደበት
ምን ፡ ግድፈት ፡ ሊገኝበት ፡ ምን ፡ ግድፈት ፡ ሊገኝበት
ወጥቷል ፡ እና ፡ ካንተ ፡ አንደበት
ምን ፡ ስህተት ፡ ሊገኝበት
ወጥቷል ፡ እና ፡ ካንተ ፡ አንደበት
በቃልህ ፡ ተናገረኛ
እኔም እሰማሀለው ፡ ዝምአትበለኛ
በለኛ ፡ ተናገረኛ
እኔም ፡ ሰማሀለው ፡ ዝም ፡ አትበለኛ
ምድረበዳ ፡ አናውጦ ፡ ዝግባን ፡ የሚቆርጥ
የሌለን ፡ እንዳለ ፡ ጠርቶ ፡ የሚለውጥ
ቅዱሳኑን ፡ ልብ ፡ በሃይል ፡ የሚያስታጥቅ
አረ ፡ እኔ ፡ ናፈቀኝ ፡ በድምፅህ ፡ መጥለቅለቅ
በለኛ ፡ ተናገረኛ ፡ እጠብቅሃለው ፡ ዝም ፡ አትበለኛ
በለኛ ፡ ተናገረኛ ፡ እታዘዝሃለው ፡ ዝም ፡ አትበለኛ
እታዘዝሃለው ፡ ዝም ፡ አትበለኛ
እታዘዝሃለው ፡ ዝም ፡ አትበለኛ
እጠብቅሃለው ፡ ዝም ፡ አትበለኛ
በህይወት ፡ እኖራለው ፡ ዝም ፡ አትበለኛ