አምላካችን ፡ ይህ ፡ ነው ፡ የምንገዛለት
ፊቱ ፡ ደፋ ፡ ቀና ፡ ዘዉትር ፡ ምንልለት
እድሜ ፡ ዘመናችን ፡ የተሰጠንለት
እግዚአብሔር ፡ አምላካችን
ለመንግስቱ ፡ ሁሉ ፡ ሚገዛለት
አምላካችን ፡ ድንቅ ፡ ነው
ከቃላትም ፡ በላይ ፡ ነው
አምላካችን ፡ ድንቅ ፡ ነው
ከመታወቅ ፡ ያለፈ ፡ ነዉ
ያለ ፡ ሚኖር ፡ ስሙ ፡ የሆነዉ
አልፋ ፡ ኦሜጋ ፡ እኔነኝ ፡ ያለው
በፅድቅ ፡ እውነት ፡ መንበሩን ፡ ያጸና
በክብር ፡ ሐይል ፡ በሞገስ ፡ በግርማ
ሊያይ ፡ ማንም ፡ በማይደፍረው ፡ ብርሃን
በክብር ፡ ያለ ፡ በዘላለም ፡ ዙፋን
ጥበብ ፡ እውቀት ፡ ማስፈራት ፡ ተጎናጽፏል
ሰማይን ፡ ያለ ፡ ምሶሶ ፡ ያቆመው
የምድር ፡ ስፋት ፡ ልኬት ፡ የወሰነው
ለባሕሩ ፡ ገደብ ፡ ያኖረለት
ለብርሀናት ፡ መንገድ ፡ ያበጀለት
ንፋስን ፡ ከመዛግብቱ ፡ ያወጣል
ደመናት ፡ ላይ ፡ ውሃን ፡ ይጭናል
ፍጥረት ፡ ሁሉ ፡ እሱን ፡ ይታዘዛል
ከመታወቅ ፡ ያልፋል ፡ የአንተ ፡ ማንነት
እጅህ ፡ ስራ ፡ የሰው ፡ ልጅ ፡ እንዴት ፡ ሊደርስበት
እጹብ ፡ ድንቅ ፡ እንጂ ፡ ሌላ ፡ ምን ፡ እንበልህ
ከአእምሮአችን ፡ በላይ ፡ እጅግ ፡ ከፍ ፡ ያልክ ፡ ነህ
ለዘመንህ ጅማሬ ፡ የለህ
ለመገኘትህ ወሰን ፡ የለህ
ለእውቀትህ ገደብ ፡ የለህ
ለሓይልህ ወደር ፡ የለህ
ለዘመንህ ፍፃሜ ፡ የለህ
ለመገኘትህ ወሰን ፡ የለህ
ለእውቀትህ ገደብ ፡ የለህ
ለሓይልህ ወደር ፡ የለህ
እንዴት ፡ ድንቅ ፡ ነህ
እንዴት ፡ ግሩም ፡ ነህ
አንተን ፡ የሚመስል
ማንም ፡ የለም