እጠጋሀለው (Etegahalew) - ሐምሌት ፡ በልጁን

ሐምሌት ፡ በልጁን
(Hamlet Beljun)

፩
(1)

እለምንሃለሁ
(Eleminihalew)

ዓ.ም. (Year): 2019
ቁጥር (Track):

፬ (4)

ርዝመት (Len.): 6:13
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሐምሌት ፡ በልጁን ፡ አልበሞች
(Albums by Hamlet Beljun)

ነብሴ ፡ በዛለች ፡ ጊዜ ፡ እግዚያብሄር ፡ ሆይ ፡ አሰብኩህ
እግዚያብሄር ፡ ሆይ ፡ አሰብኩህ
ክፉ ፡ ቀኖች ፡ ከፊቴ ፡ በመጡብኝ ፡ ሰአት
አዳኜ ፡ ሆይ ፡ አሰብኩህ
እግዚያብሄር ፡ ሆይ ፡ አሰብኩህ

የጠላቶቼ ፡ ሀይል ፡ እጅጉን ፡ በርትቶ
ሊውጠኝ ፡ ሚፈልግ ፡ ሲዞረኝ ፡ አብዝቶ
በጨነቀኝ ፡ ጊዜ ፡ ስምህን ፡ ጠራሁት
ከመቅደስህ ፡ ቃሌን ፡ ሰማህ ፡ የኔን ፡ ጩኸት
በበዛው ፡ ድካሜ ፡ ገለጥክ ፡ ብርታትህን
ከወደረኛዬ ፡ ይልቅ ፡ አብዝተህ ፡ አቅሜን

ስለዚህ ፡ ሁልጊዜ ፡ እጠጋሀለው
ትድግናህ ፡ ደህንነትም ፡ ካንተ ፡ ዘንድ ፡ ነው
በምትገኝበት ፡ እፈልግሀለው
ስለዚህ ፡ አብዝቼ ፡ እጠጋሀለው

ደግሞ ፡ ስጠጋህ ፡ ሀዘኔ ፡ በደስታ
ደግሞ ፡ ስጠጋህ ፡ መቅበዝበዝን ፡ በእርጋታ
ደግሞ ፡ ስጠጋህ ፡ እምነትን ፡ በስጋት ፡ ፋንታ
ቀይረኸዋል ፡ ክበርልኝ ፡ የኔጌታ

ካደከመኝ ፡ ይልቅ ፡ የምታበረታኝ
ካስፈራራኝ ፡ ይልቅ ፡ የምታስመካኝ
ካጨለመብኝ ይልቅ ፡ የምታነጋው
እንድትልቅ ፡ አውቃለው ፡ መደገፌም ፡ ባንተ ፡ ነው

እጅህ ፡ እጄን  ስለያዘው ፡ አርፌአለው
እኔም ፡ የአቅሜን ፡ ሙጥኝ ፡ እልሀለው
የዘላለም ፡ ክንድህ ፡ ከበታቼ ፡ ነው
ምህረትህ ፡ ቸርነትህ ፡ ዋስትናዬ ፡ ነው

ደግሞ ፡ ስጠጋ ፡ ፍርሀቴን አጀግነሀል
ደግሞ ፡ ስጠጋህ ፡ ልቤን ፡ በቃልህ ፡ ደግፈሀል
ደግሞ ፡ ስጠጋህ ፡ እጆቼን ፡ ሰልፍ ፡ አስተማርክ
አሸናፊ ፡ አረከኝ ፡ የጠላቴን ፡ ጀርባ ፡ ሰጠህ

እግዚያብሄር ፡ አለቴ
አምባዬ ፡ ነህ ፡ መድሀኒቴ
ደግ ፡ ልብህ ፡ ያስጠጋል
መልካም ፡ ክንድህ ፡ ያስመካል

እጠጋሀለው(3) ሰላሜ ፡ ባንተ ፡ ነው
እጠጋሀለው(3) እረፍቴ ፡ ባንተ ፡ ነው
እቀርብሀለው (4)ሰላሜ ባንተ ፡ ነው
እቀርብሀለው (4) ደስታዬ ፡ ባንተ ፡ ነው