አንተማ ፡ ፍቅር ፡ ነህ ፡ የማትለዋወጥ
መውደድህ ፡ ፍፁም ፡ ነው ፡ ብርቱ ፡ ማይናወጥ
የመስቀሉ ፡ ስራ ፡ ምስክር ፡ ነው
የፍቅር ፡ ልክህን ፡ ጥጉን ፡ ያሳየው
ቀረጽከኝ ፡ በመዳፍ ፡ ላትጥለኝ ፡ ዘላለም
ባንተ ፡ በኩል ፡ እኔ ፡ ስጋት ፡ የለኝም
እኔ ፡ ምፈራው ፡ እኔን ፡ ነው
የምህረትህ ፡ ጥላህን ፡ እንዳለምደው
የቆምኩ ፡ መስሎኝ ፡ እንዳልወድቅ
ከሕያው ፡ ምንጩ ፡ ጋር ፡ ካለቱ ፡ ልጣበቅ
አረ ፡ እኔ ፡ ማላምነው ፡ እኔን ፡ ነው
የያዘኝ ፡ እጅህን ፡ እንዳልገፋው
የቆምኩ ፡ መስሎኝ ፡ እነዳልወድቅ
ከሕያው ፡ ምንጩ ፡ ጋር ፡ ካለቱ ፡ ልጣበቅ
የምወደው ፡ ልጄ ፡ እሱ ፡ ነው ፡ ባልከው
በኢየሱስ ፡ እለምንሃለሁ
እራሱን ፡ ባዶ ፡ አርጎ ፡ ከላይ ፡ በመጣዉ
በኢየሱስ ፡ እለምንሃለሁ
ሁሉ ፡ በሁሉ ፡ ሆኖ ፡ ዝቅ ፡ ዝቅ ፡ ባለው
በኢየሱስ ፡ እለምንሃለሁ
የፈቃድህን ፡ ጽዋ ፡ ጭልጥ ፡ ባደረገው
በኢየሱስ ፡ እለምንሃለሁ
በፊትህ ፡ ሊያቀርበኝ ፡ እንደ ፡ ደም ፡ ላብ ፡ ባላበው
ስለ ፡ ኢየሱስ ፡ እለምንሃለሁ
ታዞ ፡ በመስቀል ፡ ላይ ፡ ነፍሱን ፡ በሰጠው
ስለኢየሱስ ፡ እማፀንሃለሁ
ልመናዬም ፡ ፀሎቴ ፡ ይህ ፡ ነዉ
በቤትህ ፡ ሁሌ ፡ እንድኖር ፡ ነው
እባክህ ፡ ብዬ ፡ ምጠይቅህ
ፍጻሜ ፡ እንዲያምር ፡ በፊትህ
እባክህ ፡ ብዬ ፡ ምለምንህ
ህይወቴ ፡ እንዲያምር ፡ በቤትህ
ዕድሜዬን ፡ በሃዘን ፡ ከመያስጨርሰኝ
ከክፉ ፡ ውሳኔ ፡ እባክህ ፡ ጠብቀኝ
ሕይወቴን ፡ አጉብጦ ፡ ከሚያወርድ ፡ መቃብር
ከጠማማ ፡ እርምጃ ፡ ሰውረኝ ፡ እግዚአብሔር
እንዳልገኝ ፡ በክፎች ፡ ማህበር
አይመረኝ ፡ የሐጢያተኞች ፡ ወንበር
ፍጻሜው ፡ ሞት ፡ ከሆነ ፡ ተድላ
አድነኝ ፡ እባክህ ፡ ነፍሴ ፡ ሳትበላ
እባክህ ፡ ብዬ ፡ ምጠይቅህ
ፍጻሜዬ ፡ እንዲያምር ፡ በፊትህ
እባክህ ፡ ብዬ ፡ ምለምንህ
ሕይወቴ ፡ እንዲያምር ፡ በቤትህ
በሚሞት ፡ ስጋዬ ፡ ሃጥያት ፡ እንዳይነግስ
በጥርሴ ፡ ነክሼው ፡ ልመስልህ ፡ ልገስግስ
በመንገድ ፡ ሊያስቀረኝ ፡ ልሚታገለኝ ፡ ስጋ
ስለምን ፡ ምኞቱን ፡ ለመፈጸም ፡ ልትጋ
ፊትህን ፡ አትሰውርብኝ ፡ ለፍቃዴ ፡ አትተወኝ
ለማይረባ ፡ አዕምሮ ፡ አሳልፈህ ፡ አትስጠኝ
ይልቁንም ፡ መንፈስህን ፡ ሙላኝ
እሱ ፡ ነው ፡ ከግብ ፡ የሚያደርሰኝ
በኃለኛው ፡ ዘመን ፡ ፊትህ ፡ እንዳላፍር
ዘይቴ ፡ አይለቅ ፡ ከመቅረዜ ፡ ስር
እባክህ ፡ ብዬ ፡ የምለምንህ
እንዳትሰውረው ፡ ከኔ ፡ ፊትህን
አስገዛልኝ ፡ ነፍሴን ፡ ማርከህ
ተለመነኝ ፡ ስለልጅህ
ተለመነኝ ፡ ስለ ፡ ልጅህ
ተለመነኝ ፡ ስለ ፡ ልጅህ