ስለኔ ፡ ሀጥያት ፡ የሞተልኝ
ነፍሱን ፡ አሳልፎ ፡ የሰጠኝ
ከዚህ ፡ የሚበልጥ ፡ ፍቅር
ከቶ ፡ ለማንም ፡ የለም
ነፍሱን ፡ በፈቃዱ ፡ የሰጠ ፡ ለአዳም ፡ ዘር
ወደ ፡ ምድር ፡ መጣ ፡ ቤዛ ፡ ሊሆን ፡ ለአለም
ዘወትር ፡ በአብ ፡ ፊት ፡ ስለ ፡ እኛ ፡ ሚማልደው
የአዲስ ፡ ኪዳን ፡ ዋስ ፡ እየሱስ ፡ ፍቅሩ ፡ ማያረጀው
ኦ ፡ ውዴ ፡ አንተ ፡ የኔ ፡ እኔም ፡ ያንተ
ላንለያይ ፡ ኪዳን ፡ ገብተን
መሀላ ፡ አለ ፡ መሀላችን
ዘላለማዊ ፡ ነው ፡ ፍቅራችን
የወደደን ፡ መውደድ ፡ ምንኛ ፡ ቀላል ፡ ነው
በዳይ ፡ በእጁ ፡ ይዞ ፡ መማር ፡ ግን ፡ ፈታኝ ፡ ነው
በፍቅሩ ፡ አሰረኝ ፡ ይህ ፡ ሆኖ ፡ በህይወቴ
ጠላቱ ሆኜ ፡ ሳለው ፡ እየሱስ ፡ ገብቶ ፡ ቤቴ
ኦ ፡ ውዴ ፡ አንተ ፡ የኔ ፡ እኔም ፡ ያንተ
ላንለያይ ፡ ኪዳን ፡ ገብተን
መሀላ ፡ አለ ፡ መሀላችን
ዘላለማዊ ፡ ነው ፡ ፍቅራችን
ደካማ ፡ ሰው ፡ ሳለሁ ፡ ቀንበር ፡ የተጫነኝ
ወደ ፡ እኔ ፡ ነይ ፡ ብሎ ፡ ከሸክሜ ፡ አሳረፈኝ
ልቡ ፡ የዋህ ፡ ትሁት ፡ ቀንበሩም ፡ ቀሊል ፡ ነው
ፍቅሩ ፡ ጠሊቅ ፡ ውሀ ፡ ማለቂያ ፡ የሌለው
ይቅርብኝ ፡ ይቅር ፡ ያላንተ ፡ መኖር
ይቅርብኝ ፡ ይቅር ፡ ያላንተ ፡ መኖር
ይቅርብኝ ፡ ይቅር ፡ አንተ ፡ የሌለህበት
መንገዴም ፡ አይቀና ፡ ያገኘኛል ፡ ሞት