ማልዶ ፡ ስነሳ ፡ ምከውነውን
ውጥኔን ፡ ዘዉትር ፡ ፊትህ ፡ ላኑረው
ፈቃድህ ፡ በጎ ፡ ፍፁም ፡ ደስ ፡ እንዲያሰኝ
የህይወቴ ፡ መርህ ፡ ሰንደቅ ፡ ይሁነኝ
ምኞቴን ፡ ይዘህ ፡ ስትከለክለኝ
ጓዳዬ ፡ በእልልታ ፡ በአምልኮ ፡ ይድመቅልኝ
የመዳንን ፡ ቀንድ ፡ ኢየሱስን ፡ ሰጥተኸኝ
ቀረብኝ ፡ ምለው ፡ እኔኑ ፡ አሳፈረኝ
አመሰግንሃለሁ ፡ ስላልሆነው ፡ ስላልተሳካው
አመሰግንሃለሁ ፡ ሀሳብህ ፡ ሁሌ ፡ መልካም ፡ ነዉ
አመሰግንሃለሁ ፡ ያለኝ ፡ ሁሉ ፡ ማይገባኝ ፡ ነው
አመሰግንሃለሁ ፡ ያረክልኝ ፡ ብዙ ፡ ነው
እልፍ ፡ ነው ፡ ያረክልኝ ፡ ችዬም ፡ አልቆጥረው
ጥቂቱን ፡ ብትነሳኝ ፡ ልቤ ፡ እሱን ፡ ናፈቀው
በእንባዬ ፡ የሞገትኩህ ፡ ሳይሆን ፡ የቀረው
አልፎ ፡ ዞሬ ፡ ሳየው ፡ ለካ ፡ ለመልካም ፡ ነዉ
ካልሆነልኝ ፡ ያልኩት ፡ ቀርቶብኝ ፡ ጠቀመኝ
መልካም ፡ አይተህልኝ ፡ ከልክለህ ፡ አዳንከኝ
ማግኘት ፡ ብቻም ፡ አይደል ፡ ማጣትም ፡ በጎ ፡ ነው
ምኞቴ ፡ ሞልቶልኝ ፡ ቢያጠፋኝ ፡ ምን ፡ ድል ፡ ነው
አመሰግንሃለሁ ፡ ስላልሆነው ፡ ስላልተሳካው
አመሰግንሃለሁ ፡ ሀሳብህ ፡ ሁሌ ፡ መልካም ፡ ነዉ
አመሰግንሃለሁ ፡ ያለኝ ፡ ሁሉ ፡ ማይገባኝ ፡ ነው
አመሰግንሃለሁ ፡ ያረክልኝ ፡ ብዙ ፡ ነው
ፀሎቴን ፡ ስትመልስ ፡ ወዳጅ ፡ ሰበሰብኩኝ
ዝም ፡ ያልከኝ ፡ ሲመስለኝ ፡ በእንባዬ ፡ ታጠብኩኝ
ተድላን ፡ ስታጠግበኝ ፡ ከእኔ ፡ ጋር ፡ ነህ ፡ አንዳላልኩ
ያሰብኩት ፡ ሳይሞላ ፡ የተውከኝ ፡ መሰለኝ
ድምፅህ ፡ ሲርቅብኝ ፡ እስኪመስል ፡ የሌለህ
በፀጥታ ፡ ውስጥም ፡ በዝምታም ፡ አለህ
ብትሰጥ ፡ ብትነሳ ፡ ፃድቅ ፡ ነህ ፡ ትክክል
ልስማማ ፡ ከሃሳብህ ፡ ፈቃድህን ፡ ልተል
ከሃሳብህ ፡ ጋር ፡ እስማማለሁ
አንተ ፡ ያልከውን ፡ ተቀብያለሁ
ባይገባኝም ፡ የማልፍበት
ግን ፡ አውቃለሁ ፡ የአንተን ፡ መልካምነት
ግን ፡ አውቃለሁ ፡ የአንተን ፡ በጎነት
ግን ፡ አውቃለሁ ፡ የአንተን ፡ ፃድቅነት